የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት የሆኑ የብልጽግና አባላት ድምጽ ሰጥተዋል
የብልጽግና አባል የሆኑ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በዛሬ እለት ድምጽ ሰጥተዋል፡፡ የውሃ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ በዛሬው እለት ድምጽ ከሰጡት ባለስልጣናት መካከል ናቸው፡፡ ሚኒስትር ስለሺ ድምጽ ሰጡት በቦሌ ክ/ተማ ወረዳ 6፤ በምርጫ ጣቢያ አንድ ጣቢያ መርጠዋል፡፡
ሙፈሪያ ካሚል በስልጤ ዞን በመገኘት መርጠዋል፡፡ የአዲስ አምክትል ከንቲባ አዳነች አበቤ በንፋስ ሰልክ ላፍቶ ከፍለ ከተማ ብስራተ ገብርኤል አከባቢ በሚገኝ የምርጫ ጣብያ ደምጽ ሰጥተዋል፡፡
የክልል መሪዎችና ባለስልጣንትም ድምጽ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ እስካሁን የሲዳማ ክልል ፕሬዘዳንት ደስታ ሌዳሞና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት ሽመልስ አብዲሳ ድምጽ ሰጥተዋል፡፡
ኢትዮጵያ 6ኛ ዙር የተወካዮች ምክርቤትና የክልል ምክርቤት ተወካዮች ምርጫ በዛሬ እለት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ምርጫ በ673 የምርጫ ጣቢያዎች በአዲስ አበባን ጨምሮ በክልሎች እየተካሄደ ይገኛል፤ ምርጫ የማይካሄደው በሶማሌ ክልል ከምርጫ ቁሳቁስ ህትመት ጋር በተያያዘ እንዲሁም በትግራይ ክልል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ምርጫ 2013 አይካሄድም፡፡
የሶማሌ ክልልና በተለያየ ምክንያት ምርጫ የማይሰጥባቸው ምርጫ ጣቢዎች ጻግሜ 1 እንደሚካሄድ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
በምርጫ ከ38 ሚሊዮን ህዝብድምጽ ለመስጠት ተመዝግቧል፤45 የሚሆኑ የምርጫ ታዛቢዎች ምርጫውን ለመታዘብ እንዲሰማሩ ቦርዱ ገልጾ ነበር፡፡