የእስራኤል ከፍተኛ ወታራዊ አዛዥ በሰሜን ጋዛ ውስጥ ተገደለ
የእስራኤል 401ኛ ብርጌድ አዛዥ ኮልኔል ኤሳን ዳክሳ በታንኩ ላይ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት ነው የተገደለው
የእስራኤል ሃማስ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ኮልኔል ኤሳን ዳክሳ በጋዛ ውጥ የተገደለ ከፍተኛ ወታራዊ አዛዥ ነው
የእስራኤል ከፍተኛ ወታራዊ አዛዥ በሰሜን ጋዛ ጃባሊያ ውስጥ ውስጥ መገደሉ ተነግሯል።
የእስራኤል 401ኛ የብረት ለበስ ብርጌድ አዛዥ ኮልኔል ኤሳን ዳክሳ በታንኩ ላይ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት መገደሉ ተነግሯል።
ኮልኔል ኤሳን ዳክሳ በሰሜናዊ ጋዛ ጃባሊያ ውስጥ የእስራኤል ጦር ወታደራዊ ዘመቻ በሚያደርግበት ወቅት በተጠመደ ፈንጂ መገደሉም ተሰምቷል።
የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ በጉዳዩ ላይ በሰጡት መግለጫ፤ ኮልኔል ኤሳን ዳክሳ ከነበረበት ታንክ ውስጥ ወርዶ በአካባቢው ቅኝት እያደረገ በነበረበት ወቅት የተቀበረ ፈንጂ ፈንድቶ መሞቱን አስታውቀዋል።
የ41 ዓመቱ ኮልኔል ኤሳን ዳክሳ አንድ ዓመት ባስቆጠረው የእስራኤል ሃማስ ጦርነት በጋዛ ውጥ ከተገደለ ወታራዊ አዛዞች ውስጥ ከፍተኛው ነው።
ኮልኔል ኤሳን ዳክሳ 401ኛ ብርጌድ አዛዥ ሆኖ የተሾመው ከአራት ወራ በፊት ባሳለፍነው ሰኔ ወር ሲሆን፤ በጃባሊያ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ የሚደረገውን ኦፕሬሽን በመምራት ላይ እንደነበረም የእስራኤል ጦር አስታውቋል።
የእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞክ፤ ኮልኔል ኤሳን ዳክሳን “ጀግና” በማለት ያወደሱ ሲሆን፤ የዳክሳ ሞት ለእስራኤል እና ለእስራኤላውያን ከፍተኛ ጉዳት ነው ብሏል።
ኮልኔል ኤሳን ዳክሳ የእስራኤል ጦር በጋዛ ውስጥ ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመረ ወዲህ የተገደለ 358ኛ ወታር መሆኑንም ፐሬዝዳንቱ አስታውቀዋል።
በሳለፍነው ዓመት ጥቅምተ 7 በመጀመረው እና አንድ ዓመት ባስቆጠረው የእስራኤል ሃማስ ጦርት በአጠቃላይ የተገደሉ የእስራኤል ወታደሮች ቁጥር 750 የደረሰ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ ከ350 በላይ የሚሆኑት ጋዛ ውስጥ ነው የተገደሉት።
እስራኤል በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል ከሊባስ ሃማስ ጋር እያደረገች ባለው ጦርነትም እስካን 43 ወታደሮች እንደተገደሉ የእስራኤል ጦር መረጃ ያመለክታል።