የሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ከሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ጋር ተገናኙ
የዩክሬን፣ አሜሪካና ደቡብ ኮሪያ መረጃ እንደሚያመለክተው ሰሜን ኮሪያ በዩክሬን ከሩሲያ ወታደሮች ጎን ሆነው የሚዋጉ በሽዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ልካለቸ

የሩሲያና ሰሜን ኮሪያ መሪዎች ባለፈው ሰኔ ወር የወታደራዊ ትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል
የሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ከሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ጋር ተገናኙ።
የሩሲያው ፕሬዘደንት ቭላድሚር ፑቲን ከሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ባለፈው ሀሙስ መምከራቸውን ሮይተርስ የሰሜን ኮሪያውን ኬሲኤንኤ ቴሌቪዥን ጠቅሶ ዘግቧል።
ፑቲን በክሬሚሊን የፖሊት ቢሮ አባልና የወርከርስ ፓርቲ ኦፍ ኮሪያ (ደብሊውፒኬ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ጸኃፊ ከሆኑት ሪ ሂ ዮንግ እና ከፓርቲው የማዕከላዊ ማዕከላዊ ቁጥጥር ኮሚቴ ሊቀመንበር ጋር በክሬሚሊን ውይይት አድርገዋል።
ኬሲኤንኤ እንደዘገበው ፑቲን ሰሜን ኮሪያ እያደረገች ላለው ድጋፍ አመስግነዋል።
"እሱ(ፑቲን) የሩሲያና ሰሜን ኮሪያ ግንኙነት ወደ ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ያደገበትን የ2024ቱን ታሪካዊ ስምምነት በከፍተኛ ደረጃ አድንቋል" ብሏል ዘገባው።
የዩክሬን፣ አሜሪካና ደቡብ ኮሪያ መረጃ እንደሚያመለክተው ሰሜን ኮሪያ በዩክሬን ከሩሲያ ወታደሮች ጎን ሆነው የሚዋጉ በሽዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ልካለቸ።
የሰሜን ኮሪያና የሩሲያ መሪዎች የተፈራረሙት " ኮምፕሬሄንሲቭ ስትራቴጂክ ፓርትነርሺፕ ስምምነት" ከባለፈው ታህሳስ ጀምሮ ተግባራዊ ሆኗል።
ፕሬዝደንት ፑቲን ባለፈው ሴኔ ወር ፒዮንግያንግን በጎበኙበት ወቅት የተደረሰው ስምምነቱ ሀገራቱ ጥቃት በሚደርስባቸው ወቅት አንደኛቸው ለሌላኛቸው ሁሉንም አይነት መንገድ ተጠቅመው ድጋፍ እንዲያደርጉ ያስችላል።