ስማርት ስልካችን ለሚስጥራዊ ጠላፊዎች መጋለጡን እንዴት ማወቅ እንችላለን፤ መከላከያ መንገዶቹስ?
የአንድሮይድና አይፎን ተጠቃሚዎች ከሚስጥራዊ ጠላፊዎች ራስን ለመጠበቅ የሚረዱ እርምጃዎችን ይፋ ተደርጓል
ባሳለፍነው የፈረንጆቹ ዓመት ብቻ የ353 ሚሊየን ሰዎች መረጃ በሚስጥራዊ መልኩ ተዘርፏል
የአሜሪካው ብሄራዊ የደህንነት ኤጀንሲ (ኤን.ኤስ.ኤ) ስማርት ስልካችን በሚስጥር መጠለፉን የምንለይበትን እና ከመጠለፍ ለመከላከል ይረዳሉ ያላቸውን ዘዴዎች አጋርቷል።
ኤጀንሲው የሳይበር ወንጀለኞች ስማርት ስልካችንን በማጥቃት የግል መረጃዎችን ለመስረቅ ተለዋዋጭ የሆኑ የተለያዩ ዘዴዎችን ይጠቃማሉ ብሏል።
ከእነዘህም ውስጥ ዋይ ፋይ ኔትዎርኮችን፣ የስማርት ስልክ መተግበሪያዎች፣ ብሉቱዝ እና የተለያዩ ክፍተቶች ተጠቃሽ መሆናቸውን ኤን.ኤስ.ኤ አስታውቋል።
በዚህም ምክንያትተጠቃሚዎች በየጊዜው ስልካቸውን እንዲያዘምኑ እና የተለያዩ የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ሲያስጠነቅቁ ይስተዋላል።
ስታቲስታ ባወጣው ሪፖርት ባሳለፍነው ዓመት በአሜሪካ በቻ ከ535 ሚሊየን በላይ እመሪካውያን ዳታ እና የግል መረጃዎች ተዘርፈው በጠላፊዎች እጅ ገብተዋል ብሏል።
ስልካችን መጠለፉን እንዴት ማወቀት እንችላለን?
ስማርት ስልካችን በሚስጥራዊ መንገድ መጠለፉን የሚያሳዩ የተለያዩ ምልክቶች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ የካሜራ መብራት ካለእኛ እውቅና በርቶ መቆየት እንዲሁም እኛ የዘጋናቸው መተግበሪያዎች ባልጠበቅነው መልኩ ከፍት ሆኖ መገኘት ተጠቃሽ ናቸው።
በተጨማሪም የስማርት ስልካችን ባትሪ በፍጥነት የሚያልቅ ከሆነ፣ ስልካቸን ፍጥነት ከቀነስ እንዲሁም ስልኩ ከመጠን በላይ የሚግል ከሆን፣ ከእኛ ቁጥጥር ውጪ ስልካችን ላይ ያሉ መተግበሪያዎች እየተዘጉ የሚከፈቱ ከሆነ ከምልክቶቹ መካል ናቸው።
የሚስጥራዊ የሳይበር ጥቃት መከላከያ መንገዶቹ?
የአሜሪካው ብሄራዊ የደህንነት ኤጀንሲ (ኤን.ኤስ.ኤ) ቀጥለው የተዘረዘሩ እርምጃዎችን ብንወስድ መልካም ነው ብሏል።
1 ሶፍትዌሮችንና መተግበሪያዎችን ማዘመን (አፕዴት ማድረግ)
የአንድሮይድም ይሁን የአይፎን ስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች በየጊዜው የስልካቸውን ሶፍትዌሮችን እና መተግበሪያዎችን ማዘመን የመረጃ ጣላፊ ወንጀለኞች መግቢያ ቀዳዳ እንዳያገኙ ማደረግ እንደሚያስቻል ተነግሯል።
ይህንን እርምጃ መውሰድ የመረጃ ጠላፊዎች ወደ ስማርት ስልካችን መግቢያ ቀዳዳ ለማሳጣት ምርጡ መንገድ እንደሆነም ነው ኤን.ኤስ.ኤ ያስታወቀው።
2. መተግሪያዎችን ከትክክለኛ ስቶሮች ብቻ ማውረድ
የስማርት ስልክከ ተጠቃሚዎች መተግበሪያዎችን (አፕሊክሽኖችን) ወደ ስልካቸው ሲያወርድ እንደ ጎግል ፕሌይ እና አፕ ስቶር ካሉ ይፋዊ ስቶሮች ላይ ብቻ እንዲያወርዱም ይመከራል።
ይፋዊ ያልሆኑ የአፕ ስቶሮች መካከል “Aptoide፣ SlideMe፣ ACMarket እና Amazon Appstore” ይገኙበታል የተባለ ሲሆን፤ ከእነዚህ ስናወርድ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው ተብሏል።
3. ዋይፋይ እና ብሉቱዝ መዝጋት
የአንድሮይድ እና አይፎን ስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች ለመረጃ ጠላፊዎች እንደዳይጋለጡ ስልካቸውን በህዝብ ዋይፋይ ላይ ከማገናኘት መቆጠብ እንዳለባቸው ይመከራል።
የአሜሪካው ብሄራዊ የደህንነት ኤጀንሲ (ኤን.ኤስ.ኤ) በበኩሉ በክፍት የዋይ ፋይ ኔትዎርኮች ላይ ስልካቸውን የሚያገናኙ ሰዎች በሚጠቀሙበት ጊዜ ብሉቱዛቸውን እንዲዘጉ መክሯል።
ይህም የመረጃ መዝባሪዎች በዋይ ፋዩ አማካኝነት መሳሪያችንን ካገኙ በኋላ ወደ ስልካችን ለመግባት ሌሎች ተጋላጭ እና ክፍት የሆኑ መንገዶችን ስለሚጠቀሙ ነው ተብሏል።
4. ኢንሳይክሪፕትድ የሆኑ የጽሁፍና የድምጽ መላላኪያ መንገዶችን መጠቀም
ኢንሳይክሪፕትድ የሆኑ የጽሁፍና የድምጽ መላላኪያ መንገዶች የመረጃ ጠላፊዎች ወደ ስልካችን ሰርገው በመግባት የግል መረጃዎቻችን እንዳይመለከቱ ይከላከላሉ።
5. አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያዎች (ሊንኮችን) አለመክፈት
የአንድሮይድ እና የአይፎን ስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች ምንጩ ካልታወቀ የሚላኩልንን እንዲሁም አጠራጣ የሆኑ ማስፈንጠሪያዎች (ሊንኮችን) እና ልጥፎችን አለመክፈትም ኤን.ኤስ.ኤ መክሯል።
6. ስማርት ስልካችንን በየሳምንቱ ዘግቶ መክፈት (ሪቡት) ማድረግ
ስፒር ፒሽንግ እና የመሳሰሉ የሰርጎ ገቦች ጠለፋን ለመከላከል ስማርት ስልኮቻችንን በሳምንት ቢያንስ አንድ ጊዜ አጥፍቶ ማብራት (ሪቡት) ማድረግ ይመከራል።
ስልክን ማጥፋት ሁሉንም የተከፈቱ ድረ-ገጾች እና መተግበሪያዎችን ዳግም የሚስጀምር ሲሆን፤ ክፍት የነበረ የባንክ አካውናትችንም እንዲወጣ (ሎግ አውት) ያደርጋል፤ የሳይበር ወንጀለኞች ሚስጥራዊነት ጥቃት እንዳይፈጽሙብን ይከላከላል።