የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፊታችን ማክሰኞ ሊታሰሩ እንደሚችሉ ተናገሩ
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ነውጥን አነሳስተዋል በሚል ክስ ሊመሰረትባቸው ይችላል ተብሏል
ዶናልድ ትራምፕ ከታሰሩ ደጋዎቻቸው አመጽ እንዲያስነሱ ጥሪ አቅርበዋል
የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፊታችን ማክሰኞ ሊታሰሩ እንደሚችሉ ተናግረዋል።
ዶናልድ ትራምፕ "ትሩዝ ሶሻል" በተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ "ህገወጡ እና ሙሰኛው የማንሀተን ጠበቃ ቢሮ የፊታችን ማክሰኞ ሊያስረኝ እና ሊከሰኝ ይፈልጋል" ብለዋል።
ትራምፕ አክለውም " የሪፐብሊካን እጩ ፕሬዝድንቱን ወንጀል መስራቴን ሳያረጋግጥ ክስ ሊመሰርትብኝ እና ሊያስረኝ ማቀዳቸውን አፈትልኮ በወጣ መረጃ አውቄያለሁ" ሲሉ ንብረትነቱ የእሳቸው በሆነው ትሩዝ ሶሻል ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።
- ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬንን ጦርነት በአንድ ቀን ውስጥ ሊፈቱት እንደሚችሉ ተናገሩ
- ትራምፕ፥ የባይደን አስተዳደር በዩክሬን ምድር 3ኛውን የአለም ጦርነት ሊያስጀምር ነው ሲሉ ወቀሱ
የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከታሰሩ ደጋዎቻቸው አመጽ እንዲያስነሱ ጥሪ አቅርበዋል ነው የተባለው።
የዶናልድ ትራምፕ ቃል አቀባይ እስካሁን የእስር ማዘዣም ሆነ ማንኛውም ይፋዊ መረጃ ከየትኛውም አካል እንዳልደረሰ ለሮይተርስ ተናግረዋል።
እንደ ዘገባው ከሆነ በትራምፕ ላይ ከሶስት ዓመት በፊት በካፒቶል አዳራሽ ደጋፊዎቻቸውን ለሁከት አነሳስተዋል በሚል ክስ ይቀርብባቸዋል ተብሏል።
እንዲሁም ለአንዲት የወሲብ ፊልም ባለሙያ በከፈሉት ከፍተኛ ገንዘብ ምክንያትም ተጨማሪ ክስ ሊመሰረትባቸው እንደሚችልም ተገልጿል
በዶናልድ ትራምፕ ላይ ምርመራ የተጀመረው በ2024 በሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ዳግም እንደሚወዳደሩ ፍንጭ መስጠታቸውን ተከትሎ እንደሆነ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ኬቪን ማካርቲ በበኩላቸው የኒዮርክ አቃቢ ህግ ቢሮ ምርመራን ተችተዋል።
ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካንን ከፈረንጆቹ 2016 እስከ 2020 ባሉት አራት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት መርተዋል።
በ2020 በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በጆ ባይደን ተሸንፈው ስልጣናቸውን ያስረከቡ ቢሆንም ምርጫው ተጭበርብሯል በሚል ውጤቱን ተቃውመው ነበር።