የሩሲያ እና የአረብ ኢምሬትስ መሪዎች ከጦርነቱ በኋላ ሲነጋገሩ የመጀመሪያቸው ነው
የአቡዳቢ አልጋወራሽ እና በአረብ ኤምሬቶች (ዩኤኢ)ምክትል የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሼህ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አልነሃያን ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ጋር መወያየታቸው ተገለጸ፡፡
ሼህ ሞሃመድ ቢን ዛይድ እና ቭላድሚ ፑቲን የዩክሬን እና የሩሲያ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ሲነጋገሩ የመጀመሪያ ነው፡፡ ሼክ መሐመድ አሁን ላይ በዩክሬን ያለው ቀውስ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ቢፈታ ለሁሉም ወገኖች ዋስትና እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡
የአቡዳቢ አልጋወራሽና የየተባበሩት አረብ ኤምሬቶች (ዩኤኢ)ምክትል የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሼህ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አልነሃያን እና የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭለድሚር ፑቲን በቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል ተብሏል፡፡
ሼክ ቢንዛይድ አሁን ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ እንደተሰጣቸው ተገልጿል፡፡ ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ እና ነዳጅ ላኪ ሀገራት (ኦፔክ) መካከል ያለውን ትብብር በተመለከተ ውይይት አድርገዋል ተብሏል፡፡ ሁለቱ ወገኖች የተስማሙት ዓለም አቀፍ የኢነርጅ ገበያ እንዲረጋጋ ስምምነት ላይ ደርሰዋልም ነው የተባለው፡፡
ሼክ ቢንዛይድ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት በተጨማሪም ከብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እንዲሁም ከፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር መነጋገራቸው ተሰምቷል፡፡
አረብ ኢምሬትስ በዩክሬን ያለው ቀውስ እልባት እንዲያገኝ ከሁሉም ወገኖች ጋር እንደምትሰራም አስታውቃለች፡፡
ከተጀመረ ስድስተኛ ቀን በያዘው የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ዩክሬናዊን ፖላድን ጨምሮ ወደ ተለያዩ የጎረቤት ሀገራት ተሰደዋል፡፡ የሩሲያ ጦር በዩክሬን የተለያዩ ግዛቶች ጦርነት የከፈተ ሲሆን አሁንም ዋና ከተማዋን ኪቪን ለማጣቃት እየተቃረበ ነው ተብሏል፡፡