አሸናፊው ግራ ዘመም ፓርቲ በአብላጫ ቢያሸንፉም መንግስት መመስረት አይችልም
አሸናፊ ያልታወቀበት የፈረንሳይ ምርጫ
ከሶስት ሳምንት በፊት በተካሄደ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ምርጫ ላይ ስልጣን የተቆጣጠሩት የኢማኑኤል ማክሮን ፓርቲ ከባድ ሽንፈት ደርሶበት ነበር፡፡
በዚህ ምርጫ ውጤት የተበሳጩት ፕሬዝዳንት ማክሮን የሀገሪቱ ምክር ቤት እንዲበተን እና አዲስ የምክር ቤት ምርጫ እንዲደረግ ወስነውም ነበር፡፡
ይህን ተከትሎም በፈረንሳይ የህግ አውጪ ምክር ቤት ምርጫ የተካሄደ ሲሆን ሁለተኛው ዙር ምርጫው ትናንት ተደርጓል፡፡
ዛሬ ፋ በተደረገው የምርጫ ውጤት ኒው ፖፑላር ፍሮንት ወይም (ኤንፒኤፍ) የተሰኘው የግራ ዘመም ፓርቲዎች ጥምረት አብላጫውን ወንበር ማሸነፍ ችሏል፡፡
ኤንፒኤፍ ፓርቲ 171 መቀመጫዎችን የፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ፓርቲ 152 እንዲሁም ስደተኛ ጠል የሚባሉት የማሪን ለፐን ፓርቲ ናሽናል ራሊ ፓርቲ ደግሞ 134 መቀመጫዎችን አሸንፈዋል፡፡
ይህን ተከትሎም በምርጫው አብላጫ ወንበሮችን ያገኘ እና መንግስት መመስረት የሚያስችል ውጤት ያላገኙት ፓርቲዎች የግድ ወደ ድርድር ለመቀመጥ እና ስልጣን ለመከፋፈል ይገደዳሉ፡፡
ፈረንሳይ የወንድ የዘር ፍሬ እጥረት እንደገጠማት ገለጸች
ይህን ተከትሎም በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዝዳንት ማክሮን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ጋብሪኤል አታል ስልጣን ሊያጡ እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡
በፈረንሳይ ህገ መንግስት መሰረት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ከተለያዩ ፓርቲዎች መሆን እንደሚችሉ ይፈቅዳል፡፡
ፈረንሳይ የገጠማት የፖለቲካ አለመረጋጋት የፓሪስ ኦሎምፒክን ልታስተናግድ ሶስት ሳምንት ብቻ እየቀራት መሆኑ ደግሞ ስጋት ፈጥሯል፡፡