ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በበኩላቸው "አትደናገጡ የአሜሪካ ባንክ ስርዓት ጤናማ ነው" ብለዋል
ለቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ብድር በማቅረብ የሚታወቀው የአሜሪካው ሲልከን ቫሊ ባንክ ከሰረ።
ዋና መቀመጫውን ካሊፎርኒያ ያደረገው የአሜሪካው ሲልከን ቫሊ ባንክ መክሰሩ ተገልጿል።
ለአሜሪካ እና አውሮፓ ግዙፍ ኩባንያዎች ብድር በማቅረብ ስመጥር የሆነው ይህ ባንክ መክሰር በርካቶችን አስደንግጧል።
የበይነ መረብ ጥቃት፣ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ገበያው ደርቶላቸው የነበሩ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አሁን ላይ ገቢያቸው መቀነሱ እና የዋጋ ግሽበት ለባንኩ መክሰር ዋነኞቹ ምክንያቶች እንደሆኑ ብሉምበርግ ዘግቧል።
በባንኩ መክሰር ምክንያት አሜሪካዊያን መደናገጥ እንደገጠማቸው መገለጹን ተከትሎ የፕሬዝዳንት ጆ ባይደ. አስተዳድር ባንኩን ለመታደግ ጥረት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን "የወቅቱ አሜሪካ ባንክ ስርዓት አስተማማኝ ነው" ያሉ ሲሆን መንግታቸው ሲልከን ቫሊ ባንክን ህልውና ለመታደግ ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆናቸውንም አክለዋል።
ይህ በዚህ እንዳለም የብሪታንያ መንግስትም ለዚህ ባንክ ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ለብዙሃን መገናኛዎች ተናግረዋል ።
ሲልከን ቫሊ ባንክ ኪሳራ ላይ መሆናቸውን ተከትሎ ገንዘባቸውን በባንኩ ውስጥ ያስቀመጡ ኩባንያዎች እና ግለሰቦችም ጭንቀት ውስጥ መግባታቸውን ገልጸዋል።
ባንኩም ገንዘባቸውን ማውጣት ለሚፈልጉ ደንበኞቹ መክፈል በማይችልበት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።
የባንኩን መክሰር ተከትሎም በርካታ ዓለም አቀፍ ባንኮች ሲልከን ቫሊ ባንክን ለመግዛት ጥያቄ በማቅረብ ላይ እንደሆኑ ተገልጿል።