ህይወትን ቀለል አድርጎ መምራት ረጅም ዕድሜ ለመኖር ያለው ጠቀሜታ
ማህበራዊ ግንኙነት ማጠናከር እና ከምንወዳቸው ጋር ጊዜ ማሳለፍም እንዲሁ ደስተኝነታችንን ይጨምራል
ሰራዎችን እና ግዴታዎችን ማጠናቀቅ ለማረፍ፣ ለመዝናናት እና የሚያስደስቱን ነገሮችን ለመከወን ጊዜ ይኖረናል
ህይወትን ቀለል አድርጎ መምራት በጤናችን ላይ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ስለሚያሳድር በተዘዋዋሪ ረጅም እድሜ እንድንኖር ያደርጋል።
ህይወትን ቀለሌ አድርጎ መምራት ማለት ጭንቀትን ማስወገድ፣ የአኗኗር ዘይቤን ቀለል ማድረግ እና ሙሉነትን እና ደስታን በሚሰጡ ተግባራት ላይ ማተኮርን ይጨምራል።
እነዚህ ተግባራት የተሻለ የአእምሮ እና ሰውነት እንዲኖር ሰለሚያደርጉ ረጅም እና ጤናማ ህይወት እንዲኖረን የማድረግ እድል አላቸው። ለምሳሌ አላስፈላጊ ነገሮችን በመቀነስ የተረጋጋ የመኖሪያ አካባቢ እንዲኖር ለማድረግ እና ጭንቀት ለመቀነስ ይረዳናል።
ሰራዎችን እና ግዴታዎችን ማጠናቀቅ ለማረፍ፣ ለመዝናናት እና የሚያስደስቱን ነገሮችን ለመከወን ጊዜ ይኖረናል። ማህበራዊ ግንኙነት ማጠናከር እና ከምንወዳቸው ጋር ጊዜ ማሳለፍም እንዲሁ ደስተኝነታችንን ይጨምራል።
ከዚህ በተጨማሪም ህይወት ቀለል አድርጎ መምራት የተመጣጠነ ምግብ መመገብን፣ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግን እና በቂ እንቅልፍ ማድረግ ማካተት ይገባዋል። እንዲህ አይነት ልምዶች በጤናችን ላይ የራሳቸው ሚና ስለሚኖራቸው እድሜ እንዲረዝም አስተዋጽኣ ያበረክታሉ።
ህይወትን ቀለል ማድረግ ብቻ ረጅም እድሜ ለመኖር ዋስትና ይሆናል ብሎ መደምደም ግን አይቻልም።