ፕሬዝዳንት አል ሲሲ ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከግብፅና ከሱዳን ጋር ህጋዊ ስምምነት ላይ እንድትደርስ ጥሪ አቀረቡ
የቻይና እና ገልፍ ሀገራት ጉባዔ በሳዑዲ አረቢያ ተካሂዷል
የግብጽ ፕሬዝዳንት አልሲሲ በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለኢትዮጵያ ጥሪ አቅርበዋል
ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ህጋዊ ስምምነት ላይ እንዲደረስ በሶስትዮሽ ውይይት በቅንነት እንድትሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።
የቻይና እና ገልፍ ሀገራት ጉባዔ የቻይና ፕሬዝዳነት ዢ ጂንፒንግ እና የገልፍ ሀገራት መሪዎች በተገኙበት በሳዑዲ አረቢያ ተካሂዷል።
በጉባዔው ላይ የተገኙት የግብጹፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ በተለያዩ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ንግግር ድርገዋል።
ፕሬዝዳንቱ በግብጽ በተካሄደው ኮፕ 27 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ እንዲሁም በዓለም ላይ እያጋጠመ ስላለው የምግብ ቀውስ በንግግራቸው ካነሱት መካከል ነው።
ፐሬዝዳንቱ በንግግራቸው ያነሱት ሌላኛው ጉዳይ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ስላለችው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ነው።
በዚህም ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ህጋዊ ስምምነት ላይ እንዲደረስ በሶስትዮሽ ውይይት በቅንነት እንድትሳተፍ በድጋሚ ጥሪ እናቀርባለን ብለዋል።
ግብፅ እና ሱዳን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሙሌትና አስተዳደር በተመለከተ ከአሳሪ የሶስትዮሽ ስምምነት ላይ እንዲደረስ ፍላጎት እንዳላቸው በተለያዩ ጊዜያት ፍላጎታቸውን ሲያንጸባርቁ ቆይተዋል።
ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በግድቡ አስተዳደር ጉዳይ የሶስትዮች ንግግር እና ድርድር ከመጀሩ ቆይተዋል፤ ነገርግን እስካን ከስምምነት አልደረሱም።
የኢትዮጵያ መንግስት ግድቡን እየገነባ ያለው ለልማት አላማ ብቻ መሆኑን እና በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ የጎላ ተጽእኖ እንደማያደርስ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። ግብጽና ሱዳን ግን በግድቡ ዙሪያ የየራሳቸው አቋም አላቸው።
በተለይም ግብጽ በቅኝ ግዛት ዘመን የተፈረመ ስምምነትን ጭምር በመጥቀስ፤ ታሪካዊ የሆነ የውሃ ድርሻዋ ላይ ተጽእኖ እንሚያሳድር እና ግድቡ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚያሳድርባት ትገልጻለች።
በ2013 ዓ.ም በአሜሪካ ዋሽንግተን ሲደረግ የነበረው የሶስትዮሽ ድርድር ከፈረስ በኋላ ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት አመቻችነት እንዲካሄድ ተስማምተዋል።
ድርድርሩ ወደ አፍሪካ ህብረት የመጣው ኢትዮጵያ፤ ድርድሩ ሳይጀመር የታዛቢነት ሚና የነበራቸው አሜሪካና የአለም ባንክ ሚናቸውን ወደ አደራዳሪነትና ወደ የስምምነት ሰነድ አርቃቂነት ከፍ በማድረጋቸው እና ኢትዮጵያም ይህን አልቀበልም በማለቷ ነው።
ኢትዮጵያ የግድቡ ጉዳይ የልማት ጉዳይ ነው ብትልም ፤ግብጽና ሱዳን የግድቡን ጉዳይ የጸጥታ ጉዳይ ነው በማለት ለተመድ የጸጥታው ም/ቤት በማቅረብ ም/ቤቱ ወይይት አድርጎበት ያውቃል።