ዛሬ ሥራ የጀመረው ሁለተኛው ዩኒት 270 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም አለው
ሲጠናቀቅ ከአፍሪካ ትልቅ ግድብ እንደሚሆን የሚጠበቀው ታላቁ የህዳሴ ግድብ 2ኛው ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በቤንሻንጉል ጉሙዝ ጉባ ወረዳ በታደሙበት ዝግጅት ነው በዛሬው ዕለት ሁለተኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት የጀመረው።
የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ካሉት 13 ተርባይኖች መካከል ዩኒት 9 የሚባለው ሁለተኛው ተርባይን የተሳካ ተከላ እና ሙከራ ከተደረገ በኋላ ኃይል የማመንጨት ስራው ን ዛሬ በይፋ ጀምሯል።
ዛሬ በይፋ ሥራ የጀመረው ሁለተኛው ዩኒት 270 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተገልጿል።
ባሳለፍነው የካቲት ወር 2014 ዓ.ም በዚህም ግድቡ ካሉት ተርባይኖች ውስጥ አንዱ የሆነው እና ዩኒት 10 የሚል መጠሪያ ያለው ተርባይን 270 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ይታወሳል።
ይህን ተከትሎም ታላቁ የኢትዮጵ ህዳሴ ግድብ የዛሬውን ጨምሮ በአጠቃላይ 540 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በማብሰሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ዘንድሮ 22 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ገደማ ውሃ መያዝ የሚያስችል እና ሁለት ተርባይኖችን ማንቀሳቀስ የሚያስችል ስራ መሰራን አስታውቀዋል
“ሆኖም የታችኛው ተፋሰስ ሀገራተ ላይ የውሃ እጥረት እንዳያግጥም ኢነርጂ እያመነጨን በታቸኛው ቦተም አውት ሌት በኩል ውኃ በከፍተኛ ሁኔታ አንድም ቀን ሳይቋረጥ እንዲሄድ እየተደረገ ነው” በለዋል።
“የሚፈሰውን ውሃ ብንይዝ ኖሮ በአጠረ ጊዜ ውስጥ ውሃ መሙላት ይቻል ነበረ ነገር ግን የኛ ፍላጎት የመልማት ብ መሆኑን ለማሳየት ውሃ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት እየለቀቀች ነው” ብለዋል።
“በረዘመ ጊዜ ውስጥ ውጃ የምንሞላው የታችኛው ተፋሰስ ሀጋርተ ሳይጎዱ እኛም ሳንጎዳ በጋራ ለመልማት ያለንን ፍላጎት ተረድተው በንግግር እና በድርድር ውጤት እንደሚመጣ እንዲተጉ” ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ግድብ ለመገንባት የመረሰት ድንጋይ ካስቀመጠች አንድ አመት በኋላ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ግብጽና ሱደን በግድቡ ላይ ስጋት እንዳላቸው ጥያቄ አንስተዋል፡፡
ኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብጽ በግድቡ አስተዳደር ጉዳይ የሶስትዮች ንግግር እና ድርድር ከመጀሩ ቆይተዋል፤ ነገርግን እስካን ከስምምነት አልደረሱም፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ግድቡን እየገነባ ያለው ለልማት አላማ ብቻ መሆኑን እና በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ የጎላ ተጽእኖ እንደማያደርስ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል፡፡ ግብጽና ሱዳን ግን በግድቡ ዙሪያ የየራሳቸው አቋም አላቸው፡፡
በተለይም ግብጽ በቅኝ ግዛት ዘመን የተፈረመ ስምምነትን ጭምር በመጥቀስ፤ ታሪካዊ የሆነ የውሃ ድርሻዋ ላይ ተጽእኖ እንሚያሳድር እና ግድቡ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚያሳድርባት ትገልጻለች፡፡
በ2013 ዓ.ም በአሜሪካ ዋሽንግተን ሲደረግ የነበረው የሶስትዮሽ ድርድር ከፈረስ በኋላ ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት አመቻችነት እንዲካሄድ ተስማምተዋል፡፡
ድርድርሩ ወደ አፍሪካ ህብረት የመጣው ኢትዮጵያ፤ ድርድሩ ሳይጀመር የታዛቢነት ሚና የነበራቸው አሜሪካና የአለም ባንክ ሚናቸውን ወደ አደራዳሪነትና ወደ የስምምነት ሰነድ አርቃቂነት ከፍ በማድረጋቸው እና ኢትዮጵያም ይህን አልቀበልም በማለቷ ነው።
ኢትዮጵያ የግድቡ ጉዳይ የልማት ጉዳይ ነው ብትልም ፤ግብጽና ሱዳን የግድቡን ጉዳይ የጸጥታ ጉዳይ ነው በማለት ለተመድ የጸጥታው ም/ቤት በማቅረብ ም/ቤቱ ወይይት አድርጎበት ያውቃል።