ልዩልዩ
ጥንታዊው የግሪክ ኦሎምፒክ ስፍራ በከፍተኛ የእሳት አደጋ ላይ ወድቋል ተባለ
የሃገሪቱ የባህል ሚኒስቴር ጥንታዊ የኦሎምፒክ ስፍራዎቹ በራሳቸው ሊጠበቁ የሚችሉበት የውሃ ማጠጫ ስርዓት እንዳላቸው ገልጿል
የግሪክ ጥንታዊ የኦሎምፒክ ስፍራዎች በከፍተኛ የእሳት አደጋ ላይ ወድቀዋል ተባለ
ሶስተኛ ቀኑን ያስቆጠረውና በግሪክ ያጋጠመው ሰደድ እሳት በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ ጥንታዊ የኦሎምፒክ ስፍራዎችን ከፍተኛ አደጋ ላይ መጣሉ ተነገረ፡፡
ለወትሮው በጎብኚዎች ይጨናነቅ የነበረው ጥንታዊው የኦሎምፒክ ስፍራ ከትናንት ጀምሮ ከጎብኚዎች ነጻ ሆኗልም ተብሏል፡፡
በከፍተኛ ሙቀት መቀስቀሱ የተነገረለት የእሳት ሰደድ አሁንም ጥቂት የማይባሉ የሃገሪቱን አካባቢዎች እያዳረሰ ይገኛል፡፡
የእሳት አደጋ ጊዜ ሰራተኞችም በተሽከርካሪዎች በሄሊኮፕተሮች ጭምር በመታገዝ እሳቱን ለማጥፋትና ተጎጂዎችን ለመታደግ በመስራት ላይ ናቸው እንደ ሃገሪቱ መንግስት ገለጻ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኪርያቆስ ሚጾታኪስም “እንደ ሰው የሚቻለንን ሁሉ” እናደርጋለን ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥንታዊ የኦሎምፒክ ስፍራዎቹ በሚገኙባት ኢሊያ ከተማና አካባቢዋ ጉብኝት አድርገው ነበር፡፡
በጉብኝቱ የተገኙት የሃገሪቱ የባህል ሚኒስትር ሊና ሜንዶኒ ጥንታዊ የኦሎምፒክ ስፍራዎቹ በራሳቸው ሊጠበቁ የሚችሉበት የውሃ ማጠጫ ስርዓት (watering system) እንዳላቸው ለጠ/ሚ ኪርያቆስ ሚጾታኪስ መግለጻቸውን የሃገሪቱ ዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡