ተመድ ለህይወት አስጊ የሆኑ ስድስት ስር ነቀል ለውጦችን አስጠነቀቀ
"የተያያዙ የአደጋ ስጋቶች 2023" ሪፖርት ለአደጋዎች መፍትሄ አለመስጠት ወደፊት አደጋው እንደሚያድግ አጽንዖት ሰጥቷል
በ2040 ከባድ አደጋዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በእጥፍ ይጨምራሉ ተብሎ ይጠበቃል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው ሪፖርት የሰውን ልጅ ህይወት ሊለውጡ ስለሚችሉ በማህበራዊ እና በአካባቢያዊ ስርዓቶች ላይ የሚታዩ ስድስት ስር ነቀል ለውጦችን አስጠንቅቋል።
"የተያያዙ የአደጋ ስጋቶች 2023" በሚል ርዕስ የቀረበው ሪፖርት ሰዎችን እና ምድርን ስጋት ላይ ለሚጥሉ ስድስት አደጋዎች መፍትሄ አለመስጠት ወደፊት አደጋው እንደሚያድግ አጽንዖት ሰጥቷል።
ሪፖርቱ በማህበራዊ ስነ-ምህዳር ስርዓት ውስጥ አደጋዎችን መቀነስ እና የሚጠበቀውን ተግባር መፈጸም በማይችልበት ቅጽበት ላይ መገኘትን መነሻ የስጋት ነጥብ አድርጓል።
- የሰው ልጅ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እያደረገ ያለው ጥረት በቂ እንዳልሆነ ተገለጸ
- ሁለት ቢሊዮን ያህሉ የዓለማችን ሰዎች የአየር ንብረት ለውጥ ስጋት መሆኑን እንደማይቀበሉ ተገለጸ
የስጋት ነጥቦቹ ከግለሰብ የአየር ንብረት፣ ስነ-ምህዳር፣ ከማህበረሰብ ወይም ቴክኖሎጂ እይታ አልፈው እርስ በርስ የተያያዙ ናቸው።
በዙሪያችን ያሉ ስርዓቶች እንደ ስነ-ምህዳር፣ ምግብ እና የውሃ ስርዓት ከሰዎች፣ ከሰው እንቅስቃሴ እና ኑሮ ጋር በቅርበት የተሳሰሩ ናቸው።
ስርዓቱ እየቀነሰ ሲሄድ አለመረጋጋት ቀስ በቀስ ያድጋል።
እ.አ.አ ከ1970ዎቹ ጀምሮ ከአየር ንብረት ጋር በተያያዙ አደጋዎች የሚደርሰው ጉዳት በሰባት እጥፍ ጨምሯል።
በ2022 ብቻ 313 ቢሊዮን ዶላር የዓለም ኢኮኖሚ ኪሳራ ደርሶበታል።
በ2040 ከባድ አደጋዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በእጥፍ ይጨምራሉ ተብሎም ይጠበቃል።
በተጨማሪም አደጋ የሚደርስባቸው አካባቢዎች በቁጥርም በስፋትም ያድጋሉ ተብሏል። እንደ ሰደድ እሳት እና አውሎ ንፋስ ያሉ አደጋዎች ወደ አዲስ አካባቢዎች ስለሚሸጋገር አደጋ ላይ ያሉ አካባቢዎች ቁጥር እና መጠን ሊሰፋ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።
እነዚህ ለውጦች በኢንሹራንስ ዘርፉ ላይ ተጽዕኖ እያሳደሩ ነው ሲሆን፤ የኢንሹራንስ አረቦን ከ2015 ጀምሮ በ57 በመቶ አድጓል።