የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር በአስጊ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ምክትላቸው ተናገሩ
በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የተቃጣው የግድያ ሙከራ በመላው አውሮፓ መደናገጥን ፈጥሯል
ካሊንካ አሁን ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሉበት ሁኔታ ህይወታቸውን አደጋ ላይ የሚጥል ባይሆንም አሁንም ከፍተኛ እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል
የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው የስሎቫኪያ ጠቅላይ ሚኒስትር በአስጊ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ምክትላቸው ተናገሩ።
ከአራት ቀናት በፊት የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው የስሎቫኪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት ፊኮ ያሉበት ሁኔታ አሁንም አስጊ መሆኑን ምክትላቸው በዛሬው እለት ተናግረዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የተቃጣው የግድያ ሙከራ በመላው አውሮፓ መደናገጥን ፈጥሯል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ካሊንካ፣ ፊኮ እየታከሙ ካሉበት በማዕከላዊ ስሎቫኪያ ከምትገኘው ባንስካ ባይስትሪካ ከተማ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ "አሁን ላይ ሁላችንም ትንሽ ተረጋግተናል" ሲሉ ተናግረዋል።
5.4 ሚሊዮን ህዝባ ባለት የማዕከላዊ አውሮፓዋ ሀገር ድንጋጤ በፈጠረው ጥቃት፣ የ59 አመቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ባለፈው ረቡዕ እለት በአራት ጥይት ተመትተዋል። ካሊንካ እንደተናገሩት ፊኮ ያሉበት ሁኔታ አሳሳቢ በመሆኑ ወደ ዋና ከተማ ወደሚገኝ ሆስፒታል ለማዛወር አልተቻለም።
አሁን ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሉበት ሁኔታ ህይወታቸውን አደጋ ላይ የሚጥል ባይሆንም አሁንም ከፍተኛ እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል ካሊንካ።
የግድያ ሙከራው በ20 ከመታት ውስጥ በአውሮፓ በፖለቲካ መሪ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጸመ ሲሆን አለምአቀፍ ውግዘትንም አስከትሏል።
የስሎቫኪያ ስፔሻላይዝድ ክሪሚናል ፍርድ ቤት በግድያ ሙከራ የተጠረጠረው በአቃቤ ህግ ጁራጅ ሲ. ተብሎ የተለየው ተጠርጣሪ ታስሮ እንዲቆይ አዛል።