ፖለቲካ
ስሎቫኪያ ከሩሲያ ደጋፊ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትርና ከምዕራባዊያን ደጋፊ እጩ መካከል ስትመርጥ ዋለች
ለም/ቤት ምርጫው እጩዎች አንገት ለአንገት መያያዛቸው ተነግሯል
የስሎቫኪያ ምርጫ ውጤት የአውሮፓን የጅኦፖለቲካ አውድ ሊቀይረው ይችላል ተብሏል
ስሎቫኪያዊያን ለም/ቤት ምርጫ ቅዳሜ ድምጽ ሲሰጡ ውለዋል።
ምርጫው የቀድሞ ግራ ዘመም ጠቅላይ ሚንስትር ሮበርት ፊኮ እና የምዕራባዊያን ደጋፊ የሆኑት ለዘብተኛ እጩን ፊት ለፊት አገናኝቷል።
ሁለቱ እጩዎች አንገት ለአንገት መያያዛቸው የተነገረ ሲሆን፤ አሸናፊው ስልጣን ከባለአደራ አስተዳደሩ ተቀብሎ መንግስት ለመመስረት የመጀመሪያውን እድል ያገኛል ተብሏል።
ስሎቫኪያ በሮበርት ፊኮ የሚመራ መንግስት ካቋቋመች የአውሮፓ ህብረት ዩክሬንን ለመርዳት የያዘውን አቋም ወደ ጎን ትላለች ተብሎ ይጠበቃል።
የፊኮ መመረጥ የቀድሞ የምስራቅ ኮሚንስት ሀገራት ለዘብተኝነትን ለመቀናቀንም መደላደል እንደሚፈጥር ይጠበቃል።
ሮበርት ፊኮ ሀገራቸው ለዩክሬን የምትሰጠውን ወታደራዊ እርዳታ እንደሚያቆሙ አስታውቀዋል።
ፕሮጎረሲቭ ስሎቫኪያ የተባለው ፓርቲ ካሸነፈ ደግሞ አሁን ያለውን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ የሚያስቀጥል ሲሆን፤ ዩክሬንን በመደገፍ የአውሮፓ ህብረት ፖሊሲዎችን እንደሚያራምድ ይጠበቃል።
የስሎቫኪያ ምርጫ እስከ ምሽት 4:00 ድረስ ድምጽ ከተሰጠ በኋላ፤ አሸናፊው በሰዓታት ውስጥ ይታወቃል ተብሏል።