“ስማርት ቴሌቪዥን” በበርካቶች ቤት ውስጥ ያለ ድምጽ አልባው ሰላይ
በስማርት ቲቪዎች ላይ ያሉ ካሜራና ማይክራፎን የቲቪውን ባለቤቶች ለመሰለል እየዋሉ ነው ተብሏል
ስማርት ቲቪ ተዘግቶም ቢሆን ባለቤቱን እንዲሰልል ሊያደርግ እንደሚችልም ተነግሯል
ስማርት ቴሌቪዥኞች በቀላሉ ለኢንተርኔት ሰርጎ ገቦች ድምጽ አልባ የስለላ መሳሪያ እየሆኑ መምጣታቸው ተነገረ።
መጀመሪያ በነጭ እና ጥቁር ብቻ ይታወቅ የነበረው ቴሌቪዥን አሁን ላይ እየዘመነ መጥቶ በቃለሉ ከስልክ እና ከኮምፒውተራችን ጋር እንዲሁም ከኢንተርኔት ጋር በመገናኘት ለተለያዩ ግላግሎቶች እየዋለ መጥቷል።
ታዲያ ቴክኖሎጂው እየዘመ መጥቶ አሁን ላይ “ስማርት ቴሌቪዥን” ላይ የደረሰው የቴሌቪዥን ቴክኖሎጂ በዘመነው ልክ አብሮት ስጋት ይዞ መምጣቱም እየተነገረ ይገኛል።
በዲጂታል ደህንነት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ዓለም አቀፍ ተቋም እንዳስታወቀው፤ ስማርት ቴሌቪዥኖች አሁን ላይ በቀላሉ ሰዎችን ለመሰለል ጥቅም ላይ እየዋሉ መሆኑን አስታውቋል።
በተቋሙ ተመራማሪ የሆነው አሌክሳንደር ባግሆቭ እንዳስታወቀው፤ አሁን አሁን እየወጡ ያሉ ስማርት ቴሌቪዥኖች ካሜራ እና ማይክራፎን የተገጠመላቸው ናቸው፤ ይህ ደግሞ መረጃ ጠላፊዎች የቴሌቪዥኖቹን ባለቤቶች በቀላሉ እንዲሰልሉ እያስቻሉ ነው ብለዋል።
በስማርት ቲቪ ላይ የተገጠሙ ካሜራ እና ማይክራፎኖች ቴሌቪዥኖቹ ተዘግተውም ቢሆን ባለቤቶቹን እንዲሰለሉ ያደርጋሉ ያሉት ባለሙያው፤ ይሕም ሰርጎ ገቦች ሰዎቸን ለመሰለል ስማርት ቲቪን እንደ ቀዳሚ አማራጭ እንዲጠቀሙ አድርጓል ብለዋል።
የመረጃ ጠላፊዎቹ በስማርት ቲቪዎቹ በኩል ሰርጎ በመግባት ከቴሌቪዥኑ ጋር ተገናኝተው የነበረው እንደ ስልክ እና ኮምፖውተር ያሉ መገልገያዎችንም በቀላሉ ለመጥለፍ እየቻሉ መሆኑንም ተናግረዋል።
ባለሙያው አክሎም ስማርት ቴሌቪዥን የምንገዛ ከሆነ “በመጀመሪያ ደረጃ ስማርት ቲቪው መደበኛ ቲቪ መሆኑን እና ኢንተርኔትን ለመጠቀም የሚያስችሉ መሳሪያዎች እንዳት ማወቅ አለብን ብለዋል።
ሰርጎ ገቦች በስማርት ቲቪ በኩል አድርገው ወደ መኖሪያ ኔታችን ኢንተርኔት እንዳይገቡ ለመከላከል የቴሌቭዥኑን ሶፍትዌሩን በየጊዜው ማዘመን እና ሌሎች ደህንነታቸው ያልተረጋገጠ መሳሪያዎችን ከቴሌቭዢኑ ጋር አለማገናኘትን እንደ አማራጭ አቅርበዋል።