ቴክኖ፣ ሳምሰንግ እና የአፕል አይፎን ስልኮች በአፍሪካ በብዛት ከሚሸጡት ውስጥ ቀዳሚ ናቸው
በአፍሪካ በፈረንጆቹ 2023 የስማርት ስልች ሽያጭ በከፍተኛ ሁኔታ ጭማሪ ማሳየቱን አዲስ የወጣ ሪፖርት አመላክቷል።
ቴክኖ፣ ሳምሰንግ፣ አይፎን፣ ኢንፊኒክስ እና አይ ቴል በፈረንጆቹ 2023 ላይ የአፍሪካን ገበያ በስፋት ከተቀቆጣጠሩት ውስጥ ቀዳሚዎቹ ናቸው ተብሏል።
በተለይም ቴክኖ፣ አይ ቴል እና ኢንፊኒክስ ስማርት ስልኮች በ2023 የአፍሪካ ስማርት ስልክ ገበያ ውስጥ 48 በመቶ መቆጣጠራቸውም ነው የተገለጸው።
በሪፖርቱ መሰረት ቴክኖ ስርማርት ስልክ በፈረንጆቹ 2023 ዓመት የስማርት ስልክ ገበያ ከሳምሰንግ እና አፕል በመብለጥ አንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጡም ተነግሯል።
መቀመጫውን ሆንግ ኮንግ ያደረገ እና ካውንተር ፖይንት የተባለ ምርምር ተቋም ባወጣው ሪፖርት በተጠናቀቀው ፈረንጆቹ 2023 አራተኛ ሩብ ዓመት ላይ ቴክኖ ወደ አፍሪካ የላከው የስርት ስልክ መጠን በ77 በመቶ እድገት አሳይቷል።
ይህ እድገትም ቴክኖ ሞባይል በአፍሪካ እና በመካለኛው ምስራቅ ያለው ሽያጭ ከሳምሰንግ እና አፕል እንዲበልጥ አድርጎታል።
የቴክኖ ሞባይል የአፍሪካ ገበያን እንዲቆጣተር ከረዱት ውስጥ አንደኛው ዋጋው ነው የተባለ ሲሆን፤ በተለይ ከ150 ዶላር ጀምሮ የሚሸጡት “Tecno Pop 7” እና “Camon 20 Pro” በተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝተዋል ነው የተባለው።
በሪፖርቱ በአንስተኛ ዋጋ ገበያ ላይ የሚገኙት ቴክኖ፣ አይ ቴል እና ኢንፊኒክስ ስማርት ስልኮች በ2023 የአፍሪካ ስማርት ስል ገበያ ውስጥ 48 በመቶውን የገበያ ድርሻ መቆጣጠራቸውን ሪፖርቱ አመላክቷል።
ከዚህ ውስጥ ቴክኖ 26 በመቶ ሲይዝ፣ ኢኒፊኒክስ 12 በመቶ እንዲሁም አይ ቴል 10 በመቶ ድርሻ መያዛቸውን ሪፖርቱ አመላክቷል።
ሌሎች የቻይና ስማርት ስልች የሆኑት ዛዮሚ እና ኦፖ የተባሉ ስማርት ስልኮችም በአፍሪካ ገበያ ውስጥ ከፍተኛ እድገት እያስመዘገቡ እደሆነ ተመላክቷል።