ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የምዕራባውያንን ማዕቀብና የሀገራቸውን ዕድገት ንግግር አድርገዋል
የሩሲያ የቴክኖሎጂ ልማት በምዕራባውያን ማዕቀብ እንደማይቆም የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አስታወቁ።
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዛሬ ባደረጉት ንግግር የምዕራባውያንን ማዕቀብና የሀገራቸውን ዕድገት የተመለከቱ ጉዳዮችን አንስተዋል።
ፑቲን በንግግራቸውም የሞስኮ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዕድገት እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
ፑቲን በሩሲያ ያለው የድህነት ሁኔታ እየቀነሰ እንደሆነም ነው በንግግራቸው ያነሱት። የሀገሪቱ የቴክኖሎጂ ዕድገት ምዕራባውያን ማዕቀብ ስለጣሉ እንደማጠይቆምም ነው የገለጹት።
ምንም እንኳን ምዕራባውያን ማዕቀብ ቢጥሉም የሞስኮ እድገት ግን ቀጣይነቱ አይቀሬ እንደሆነ ነው ያነሱት፡፡ የሩሲያ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አሁን ባለው መልኩ እንደሚቀጥልም ፑቲን ተናግረዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ ዛሬ በስትራቴጂክ ልማት ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ስለኮሮና ቫይረስ ማንሳታቸውም ተጠቅሷል፡፡ ምንም እንኳን ዓለም አቀፍ ጫና ቢኖርም ኮሮና ካስከተለው ችግር ለመውጣት ሀገራቸው ጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኗን ጠቅሰዋል፡፡
አሁን ላይ በሩሲያ ያለው የድህነት ደረጃ እንጅ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱንም ፕሬዝዳንቱ ጠቅሰዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም በሀገሪቱ የሞት ምጣኔ መቀነስ ማሳየቱን ጠቅሰዋል፡፡
የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን የሆነው ሩሲያ ቱዴይ እስካሁን ፕሬዝዳንቱ ተናገሯቸው ካላቸው ነጥቦች መካከል የዩክሬን ጉዳይ አልተገለጸም፡፡
ባለሙያዎች እንዳሉት በኢንዱስትሪዎች ላይ ያለው ማዕቀብ ከሶስት እስከ አምስት ዓመታት ባሉት ጊዜያት እንደሚቀለበስ ገልጸዋልም ተብሏል፡፡