ሁሉም ሀገራት ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና እንዲሰጡ የተመድ ባለሙያዎች ቡድን ጠየቁ
ይህ ጥሪ የተላለፈው ስፔን፣ አየርላንድ እና ኖርዌይ ለፍልስጤም እውቅና በመስጠት እስራኤልን ካስቆጡ በኋላ ነው
እስራኤል ለፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማሰ የልብልብ ይሰጣል በሚል እውቅና የሚሰጡ አከላትን አጥብቃ ትቃወማለች
ሁሉም ሀገራት ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና እንዲሰጡ የተመድ የባለሙያዎች ቡድን ጠየቁ።
የተመድ የባለሙያዎች ቡድን በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም እንዲሰፍን ሁሉም ሀገራት ለፍለስጤም የሀገርነት እውቅና እንዲሰጡ በትናንትናው እለት ጥሪ አቅርበዋል።
ይህ ጥሪ የተላለፈው ስፔን፣ አየርላንድ እና ኖርዌይ ለፍልስጤም እውቅና በመስጠት በጋዛ እያደረገች ባለው ጦርነት ምክንያት ከዓለም እየተገለለች ያለችውን እስራኤልን ካስቆጡ በኋላ ነው።
በፍልስጤም ግዛቶች ያለውን የሰብአዊ መብት ሁኔታ የሚከታተለው የተመድ ልዩ መልክተኛ ያካተተው ቡድኑ እውቅና መስጠት የፍልስጤማውያን መብት ማክበር ነው ብለዋል።
ቡድኑ ለፍልስጤም እውቅና መስጠት በፍልስጤም ብሎም በአጠቃላይ በመካከለኛ ምስራቅ ሰላም እንዲሰፍን ቅድመ ሁኔታ መሆኑን ገልጸዋል።
"ቱ ሰቴት ሶሉሽንስ የፍለስጤም እና የእስራኤል ደህንነት እንዲጠበቅ የሚያስችል አለምቀአፍ ስምምነት የተደረሰበት ብቸኛ አማራጭ እና ትውልጆችን ከግጭት አዙሪት የሚያወጣ ነው"
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዚህ ጉዳይ መልስ አልሰጠም።
ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና የሰጡት ሰፔን፣ አየርላንድ እና ኖርዌይ በጋዛ ተኩስ አቁም እንዲደረስ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ሶስቱ ሀገራት ውሳኔያቸው ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ተመሳሳይ ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ ያነሳሳል ብለው ተስፋ አድርገዋል።
እስራኤል ባለፈው ጥቅምት ወር ጥቃት ለፈጸመባት ለፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማሰ የልብልብ ይሰጣል በሚል እውቅና የሚሰጡ አከላትን አጥብቃ ትቃወማለች።
ሀማስን ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ ያቀደችው እስራኤል የሀማስ የመጨረሻ ምሽግ ይገኝባታል የተባለችውን በግብጽ ድንበር የምትገኘውን ራፋን እያጠቃች ነው።