አልሸባብ መቀመጫወን ሶማሊያ ያደረገና ከአል-ቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለው የሽብር ቡድን ነው
የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር እያካሄደ ባለው ዘመቻ 40 የአልሸባብ የሽብር ቡድን ታጣቂዎችን መግደሉን አስታውቋል።
የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር በመካከለኛው ሸበሌ ክልል እያካሄደ ባለው ዘመቻ የሽበር ቡድኑን ታጣቂዎች መግደሉን የሶማሊያ ብሄራዊ የዜና ኤጀንሲ ባወጣው ዘገባ አስታውቋል።
አዲሱ የሶማሊያ ፐሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃመድ ሶማሊያውያን ሽብርተኝነት በቆራጥነት እንደሚታገሉ መግለጻቸው ይታወሳል።
አሜሪካም በቅርቡ በሶማሊያ የመሸጉትንና ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸውን የአልሻባብ ተዋጊዎች ኢላማ ያደረገ የአየር ጥቃት መሰንዘሯም ይታወሳል።
አሜሪካ የወሰደቸው እርምጃ፤ ጆ ባይደን ወታደሮቻቸውን እንደገና ወደ አፍሪካ ቀንዷ ሀገረ ሶማሊያ እንደሚልኩ ካሳወቁ በኋላ የተወሰደ የመጀመሪያ እርምጃ ነው፡፡
በጥቃቱ አምስት የአልሸባብ ተዋጊዎች መገደላቸውን እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን የሶማሊያ ማስታወቂያ ሚኒስቴር በወቅቱ ገልጾ ነበር።
አልሸባብ ከአል ቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለው የሽበር ቡድን ሲሆን፤ መቀመጫውን ሶማሊያ በማድረግ ሶማሊያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የተለያዩ የወንጀል ተግባራትን ሲፈጽም የቆየ ድርጅት ነው።