መርከቧ የባንግላዲሽ ሰንደቅ አላማ በመያዝ ከሞዛምቢክ ወደ አረብ ኢምሬት በመጓዝ ለይ ነበረች
የሶማሊያ መርከብ ጠላፊዎች ላገቷት መርከብ 5 ሚሊዮን ዶላር መቀበላቸው ተገለጸ፡፡
ኤምቪ አብዱላህ የተሰኘች እቃ ጫኝ መርከብ መነሻዋን ሞዛምቢክ በማድረግ ወደ አረብ ኢምሬት በመጓዝ ላይ እያለች ነበር በሶማሊያ ባህር ላይ የታገተችው፡፡
በመጫን አቅሟ ትልቅ አቅም ያለት ይህች መርከብ የባንግላዲሽ ኩባንያ ንብረት ስትሆን ከሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ 600 ማይል ርቀት ላይ በጠላፊዎች እጅ ወድቃለች፡፡
መርከቧ በጠላፊዎች እጅ ከወደቀች በኋላ በተደረገ ድርድር 5 ሚሊዮን ዶላር ከተከፈለባት በኋላ መለቀቋን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ከመርከቧ ጋር አብረው ታግተው የነበሩ 23 የባህር ሀይል አባላት ገንዘቡ የማስለቀቂያ ገንዘቡ ከተከፈለ በኋላ ተለቀዋልም ተብሏል፡፡
ኬንያ ውጥረት የሚያረግብ የባህር ጠረፍ ስምምነት ሀሳብ ማቅረቧ ተገለጸ
እንደዘገባው ከሆነ የሶማሊያ ባህር ጠላፊዎች ለበርካታ ዓመታት መሰል አደጋ ሳያደርሱ የቆዩ ቢሆንም አሁን ላይ በህንድ ውቂያኖስ ላይ በሚደረጉ የባህር ትራንስፖርት ላይ የደህንነት ስጋት ደቅነዋል፡፡
ለባህር ጠላፊዎቹ መነቃቃት የእስራኤል-ሐማስ ጦርነት መጀመር ጥሩ እድል ፈጥሮላቸዋል የተባለ ሲሆን የሀገራት ትኩረት ወደ ቀይ ባህር መዞሩ ለሶማሊያ ባህር ጠላፊዎች ማንሰራራት ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የሶማሊያ መንግስት ስለ እገታውም ሆነ ስለ መርከብ ጠላፊዎቹ ለተጠየቀው ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧልም ተብሏል፡፡
የሶማሊያ ባህር ጠላፊዎች ከፈረንጆቹ 2008 እስከ 2018 ዓመታት ድረስ ዋነኛ ስጋት የነበሩ ሲሆን ባለፉት 8 ዓመታት ውስጥ ምንም አይነት ስጋት አልፈጠሩም ነበር፡፡