የሶማሊያ ፕሬዝዳንት የሃገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን ገደቡ
ሮብል ሃገራዊ ምርጫው እስኪጠናቅቅ ድረስ ባለሥልጣናትን የማስወገድም ሆነ የመሾም ሥልጣን እንደሌላቸውም ነው መግለጫው ያተተው
ፋርማጆ የጠቅላይ ሚኒስትሩን የአስፈጻሚነት ስልጣን አንስተዋል
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት መሃመድ አብዱላሂ መሃመድ (ፋርማጆ) የጠቅላይ ሚኒስትር መሃመድ ሁሴን ሮብልን ስልጣን ገደቡ፡፡
በፋርማጆ የተሰጠውን የገደብ ትዕዛዝ በማስመልከት የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት መግለጫ አውጥቷል፡፡
በመግለጫው ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሽግግሩን ሕገ መንግሥት ጥሰዋል”ያለ ሲሆን የአስፈጻሚነት (ኤክስኩቲቭ) ስልጣናቸው መነሳቱን አስታውቋል፡፡
ሮብል ሃገራዊ ምርጫው እስኪጠናቅቅ ድረስ ባለሥልጣናትን የማስወገድም ሆነ የመሾም ሥልጣን እንደሌላቸውም ነው መግለጫው ያተተው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሬዝዳንቱን ውሳኔ በመቃወም፤ እርምጃው የሃገሪቱን ህገ መንግስት እንደሚጥስ እና የምርጫ ሂደቱን እንደሚያስተጓጉል በማሳሰብ ፋርማጆ ጣልቃ መግባታቸውን ያቆሙ ሲሉ ዝርዝር ነጥቦችን የያዘ መግለጫ አውጥተዋል፡፡
መሪዎቹ ከቅርብ ጊዜት ወዲህ በከፋ ቅራኔ ውስጥ ነው የሚገኙት፡፡
በተለይም የሃገሪቱ ደህንነት ባልደረባ የነበረችው ኢክራም ታህሊል ደብዛ መጥፋት ጋር በተያያዘ ሮብል የሃገሪቱን የደህነት ሹም ፋሃድ ያሲን ሀጂ ጣሂርን ከሃላፊነት አንስተው ይበልጥ አቃቅሯቸዋል፡፡
የሶማሊያው ጠ/ሚ ሞሀመድ ሁሴን የሶማሊያ ብሔራዊ ደህንነት ኤጀንሲ ዳይሬክተርን ከስራ አባረሩ
ፋርማጆ ፋሃድ ያሲን ሀጂ ጣሂርን ከስልጣን መነሳት በመቃወም የብሔራዊ ደህንነት አማካሪያቸው አድርገውም ሾመዋቸዋል፡፡
ሮብል በመንግስት ወጪዎች ላይ ያለ እሳቸው እውቅና የሚፈጸሙ ነገሮች እንዳይኖሩ በመስታወቅ እገዳ ጥለው እንደነበር ይታወሳል፡፡
ይህ ቅራኔያቸው ተባብሶም ነው ዛሬ ፋርማጆ “ከስልጣኑ እያለፈ ነው” ያሉትን ጠቅላይ ሚኒስትር ሮብልን ያገዱት፡፡