የሶማሊያ ፕሬዝዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር በብሔራዊ ደህንነት ሹመት ዙሪያ ወደ ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል
የአፍሪካ ሀብረት እና ተመድ የሶማሊያ መሪዎች ልዩነቶቻቸውን በፍጥነት እንዲፈቱ አሳስበዋል
የመሪዎቹ አለመግባባት ሶማሊያን ወዳልተፈለገ ግጭት እንዳያስገባት ተሰግቷል
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር በብሔራዊ ደህንነት ሹመት ዙሪያ ወደ አለመግባባት አምርተዋል።
ፕሬዝዳንት መሀመድ ፋርማጆ እና ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሀሰን ሮቤ ወደ አለመግባባት ያመሩት በሶማሊያ ብሔራዊ ደህንነት ሃላፊ ሹመትን አስመልክቶ ነው።
መሪዎቹ ከአንድ ወር በፊት በሞቃዲሾ በተፈጸመ ግድያ ዙሪያ የአገሪቱ የደህንነት ሀላፊ ፋሃድ ያሲንን ኃላፊነቱን አልተወጣም በሚል ከስልጣን መነሳቱን ተከትሎ ነው።
- የሶማሊያ ፕሬዝዳንት የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ መሪዎችን እንዲያደራድር ጠየቁ
- የሶማሊያው ጠ/ሚ ሞሀመድ ሁሴን የሶማሊያ ብሔራዊ ደህንነት ኤጀንሲ ዳይሬክተርን ከስራ አባረሩ
ፋሃድ ያሲንን ከስልጣን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሀሰን ሮቤ የሀገሪቱ የደህንነት ተቋም የስራ ባልደረባ የደረሰበት አልታወቀም ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግም ኃላፊው ተባባሪ አይደሉም ሲሉ ተናግረዋል።
በዚህም ምክንያት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለብሔራዊ ደህንነት ተቋም ሌላ አዲስ አመራር መሾማቸውን ተከትሎ ፕሬዝዳንት መሀመድ ፋርማጆ ሹመቱ ህገ መንግስቱን የጣሰ ነው በሚል ውድቅ አድርገዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ ግን ፕሬዝዳንቱ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተባረሩትን የደህንነት ሹም የጸጥታ አማካሪያቸው አድርገው መሾማቸው የመሪዎቹን ልዩነት እንዲባባስ አድርጎታል ሲል ሲ.ጂቲ.ኤን አፍሪካ ዘግቧል።
አፍሪካ ህብረት እና የመንግስታቱ ድርጅት የሶማሊያ ከፍተኛ አመራሮች ጉዳዩን በውይይት እንዲፈቱ አሳስበዋል።
የአመራሮቹ አለመግባባት በሽበር ጥቃት እና በጎሳ ግጭት የምትታመሰው ሶማሊያን ወደ ሌላ አላስፈላጊ ግጭት እንዳይወስዳት ተሰግቷል።
ፕሬዝዳንት መሀመድ ፋርማጆ እና ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሀሰን ሮቤ ወደ አለመግባባት ያመሩት ካሳለፍነው ሚያዝያ ወር ጀምሮ ሲሆን ፕሬዝዳንቱ የስልጣን ጊዜያቸውን በ2 ዓመት ማራዘማቸውን ተከትሎ ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት ጉዳዮችን እንዲመሩ ሁለቱ መሪዎች ባደረጉት ውይይት በስምምነት ልዩነቶቻቸውን የፈቱ ቢመስልም አሁን ደግሞ መልሰው ወደ ግጭት አመርተዋል።
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተራዘመው የሶማሊያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከአንድ ወር በኋላ እንዲካሄድ ስምምነት ላይ ቢደረስም በብዙ ምከንያቶች ምርጫው በድጋሜ ተራዝሟል።