በአዲስ አበባ "የተማሪዎች ምገባ ኤጀንሲ"ሊቋቋም ነዉ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ "የተማሪዎች ምገባ ኤጀንሲ" እንዲቋቋምወሰነ፡፡
ኤጀንሲው ተጠሪነቱ ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት እንዲሆንም የወሰነዉ ካቢኔው፣ የኤጀንሲው መቋቋም በተያዘው አመት በሰፊው የተሰራውን የትምህርት መሳሪያዎች አቅርቦትና የተማሪዎች ምገባ መርሀግብር ቀጣይነት እንዲኖረው እና ተቋማዊ ሆነው እንዲቀጥሉ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡
ኤጀንሲው በየአመቱ ለተማሪዎች የሚደረጉ የቁሳቁስ ድጋፎችና የምግብ አቅርቦቶች በተቀናጀና ወጥ በሆነ መልኩ እንዲሁም ያለመቆራረጥ ለተማሪዎች እንደደርሱ የማድረግ ተልእኮን ይዟል፡፡
ለዚህም ኤጀንሲው የከተማ እስትዳደሩ ለተግባሩ የመደበውን በጀት ሰራ ላይ ከማዋል ጀምሮ ለጋሽ አካላትንና በጎ ፈቃደኞችን የማስተባበርና አቅርቦቶቹ በትክክል እየተዳረሱ መሆኑን የመቆጣጠር ኃላፊነት አለበት፡፡
አስተዳደሩ በቅርቡ ይፋ ያደረገው ለታዳጊ ሴቶች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ የማሰራጨት እቅድም በኤጀንሲው የሚመራ ይሆናል።
የኤጀንሲው መቋቋም ታዳጊዎች ትኩረታቸው ትምህርት ላይ ብቻ እንዲሆን በማድረግ የታዳጊዎች የትምህርት አቅም ላይ ከፍተኛ የሆነ አዎንታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል ተብሏል፡፡
ተማሪዎች የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንዲሁም በውጪም ይሁን በሀገር ውስጥ የነጻ ትምህርት እድል እንዲያገኙ የማድረግ ተግባር ማከናወንም ለኤጀንሲው የተሰጠ ኃላፊነት ነው የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽ/ቤት እንዳስታወቀው፡፡