ሶማሊያ ስንቅ ሰርቀዋል ያለቻቸውን በአሜሪካ የሰለጠኑ ኮማንዶዎቿን አሰረች
ባለፈው የካቲት ወር አሜሪካ በደናብ በ100 ሚሊዮን ዶላር ወጭ አምስት ወታራዊ ካምፖችን ወይም ሰፈሮችን ለመገንባት መስማማቷ ይታወሳል
የሶማሊያ መንግስት በአሜሪካ የሰለጠነው ኮማንዶ ዩኒት አባል የሆኑ በርካታ ወታደሮች በአሜሪካ ስንቅ በመስረቅ ተጠርጥረው መታሰራቸውን አስታውቋል
ሶማሊያ ስንቅ ሰርቀዋል ያለቻቸውን በአሜሪካ የሰለጠኑ ኮማንዶዎቿን አሰረች።
የሶማሊያ መንግስት በአሜሪካ የሰለጠነው የደናብ ኮማንዶ ዩኒት አባል የሆኑ በርካታ ወታደሮች በአሜሪካ የተለሰገን ሬሽን (የወታደር ስንቅ) በመስረቅ ተጠርጥረው መታሰራቸውን አስታውቋል።
የሶማሊያ መንግስት አክሎም እንደገለጸው አሜሪካ ስንቅ ብትለግስም ለወታደሮቹ ስንቅ የማከፋፈል ኃላፊነት የእሱ ነው።
የደናብ ኮማንዶ ዩኒት አሜሪካ ከአል ቃኢዳ ጋር ግንኙነት ያለውን አልሸባብን ለመዋጋት በምታደርገው ጥረት ቁልፍ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ባለፈው የካቲት ወር አሜሪካ በደናብ በ100 ሚሊዮን ዶላር ወጭ አምስት ወታራዊ ካምፖችን ወይም ሰፈሮችን ለመገንባት መስማማቷ ይታወሳል።
የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስቴር ትናንት ባወጣው መግለጫ ስርቆቱን ለአለምአቀፍ አጋሮቹ ማሳወቁን እና የደረሰበትን የምርመራ ውጤትም እንደሚያሳውቅ ግልጽ አድርጓል።
የአሜሪካ መንግስት ጉዳዩን በትኩረት እንደሚከታተለው መግለጹን ሮይርስ ዘግቧል።
እንደዘገባው ከሆነ አሜሪካ ወደፊት ሊደረጉ በሚችሉ እርዳታዎች ላይ ተጽዕኖ ሊፈጥሩ የሚችሉ ሌሎች ችግሮች እንዳይፈጠሩ ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግ እየተነጋገረች ነው።
አሜሪካ በአልሸባብ ላይ ፈጣን ጥቃት የሚያደርሱ 3000 የደናብ አባላትን ለማሰልጠን እና ለማስታጠቅ በ2017 ነበር የተስማማችው። የአል ሸባብ ቡድን ከ2006 ጀምሮ በሶማሊያ ማዕከላዊ መንግስት ይዞታቸው ውስጥ ሰርጎ በመግባት ጥቃት ሲያደርስ ቆይቷል።
አሜሪካ ለሶማሊያ መንግስት ወታደራዊ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር በቀጥታ ወታደሮቿን በመላክ ስትዋጋ ቆይታለች።