ፖለቲካ
የሶማሊላንድ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ፕሬዝደንታዊ ምርጫውን አሸነፉ
ለሰባት አመታት ሶማሊላንድን የመሩት የቀድሞው ገዥ ፓርቲ ኩልምዬ መሪ ሙሴ ቢሂ አብዲ 30 በመቶ ድምጽ በማግኘት ሁለተኛ ሆነዋል
ሶማሊሊንድ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችው የወደብ ስምምነት በሶማሊያ እና ኢትዮጵያ መካከል ውጥረት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል
የሶማሊላንድ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ፕሬዝደንታዊ ምርጫውን አሸነፉ።
የራስ ገዟ ሶማሊላንድ ተቃዋሚ መሪ ባለፈው ሳምንት የተካሄደውን ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸውን የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን በዛሬው እለት ይፋ ማድረጉን ኤፒ ዘግቧል።
የዋና ተቃዋሚው ዋዳኒ ፓርቲ መሪ አብዲራህማን ሞሀመድ አብዱላሂ ከ50 በመቶ በላይ ድምጽ ማግኘት ችለዋል።
ለሰባት አመታት ሶማሊላንድን የመሩት የቀድሞው ገዥ ፓርቲ ኩልምዬ መሪ ሙሴ ቢሂ አብዲ 30 በመቶ ድምጽ በማግኘት ሁለተኛ ሆነዋል።
ምርጫው በበጀት እጥረት እና በሌሎች ምክንያቶች ከ2022 ወዲህ ለሁለት ጊዜ መራዘሙ ይታወሳል።
ግጭት እየተካሄደ በነበረበት በ1991 ከሶማሊያ የተገነጠለችው ራስ ገዟ ሶማሊላንድ አለምአቀፍ እውቅና ባይኖራትም የራሷ መንግስት፣ መገበያያ ገንዝብ እና የራሷ የጸጥታ መዋቅር አላት። ሶማሊላንድ ከሶማሊያ ይልቅ ለአመታት የተረጋጋች ሆኗ ቆይታለች።
ሶማሊሊንድ ባለፈው የፈረንጆቹ አዲስ አመት ከጎረቤት ኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችው የወደብ ስምምነት ሉአላዊነቴ ተጥሷል በምትለው ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ መካከል ውጥረት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል።