ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃመድ አስመራ ሲደርሱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አቀባበል አድርገውላቸዋል
የሶማሊያ ፕሬዝዳት ሀሰን ሼክ መሃመድ ለያፋዊ የስራ ጉብኝት ኤርትራ መግባታቸው ተገለጸ።
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃመድ አስመራ ሲደርሱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል ነው የተባለው።
ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃመድ በአስመራ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉም የኤርትራ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃመድ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማሻሻል እንዲሁም በወቅታዊ አህጉራዊ እና አለም አቀፍ የጋራ ጉዳዮች ላይ እንደሚያዩም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃመድ ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ስምምነት በኋላ በመጀመሪያው የውጭ አገር ጉዟቸውን ነው ያደረጉት።
የሶማሊያ ፕሬዝዳት ሀሰን ሼክ መሃመድ የኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ስምምነትን ተከትሎ ከግብጽ፣ ኡጋንዳ፣ ቱርክ እና ኳታር ፕሬዝዳንቶች ጋር እንዲሁም፤ ከአውሮፓ ህብረትና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ጋር በስልክ ተነጋግረዋል።
በትናንትናው እለትም የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የደረሰችውን የወደብ ሰምምነት "ውድቅ የሚያደርግ" ህግ መፈረማቸው ተዘግቧል።