በሶማሊያ በቅርቡ በተካደው ምርጫ መሃመድ ፋርማጆ ስልጣናቸውን ለፕሬዝደንት ሐሰን ማሀሙድ አስረክበዋል
የሶማሊያ መንግስት የአልሸባብ ፕሮፓጋንዳ የሚመስሉ ይዘት ያላቸውን እርምጃ እወስዳለሁ ስትል አስጠንቃለች፡፡
ማስጠንቀቂያውን ተላልፈው የሚገኙ ሚዲያዎች እቀጣለሁ ስትል ማስጠንቀቋን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
የሶማሊያ ምክትል የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር እንደተናገሩት የአሸባሪውን የአልሸባብ ዜና ማሰራጨት መከልከሉን እና አሸባሪዎች መልእክት የሚያስተላልፉባቸው 40 የማህበራዊ ሚዲያዎች ተዘግተዋል፡፡
ምክትል ሚኒስትሩ አክለውም የአልሸባብን መልእክት የሚያስተላልፍ ማንኛውም ሚዲያ ወይም ግለሰብ አንደሚያዝ ገልጸዋል፡፡
አልሸባብ በሶማሊያ በበርካታ ግዛቶች የሚንቀሳቀስ እና በሶማሊያ መንግስትን ለመገልበጥ ለአስርት አመታት ሲዋጋ ቆይቷል፡፡
አልሸባብን ለሟዋት የአፍረካ ህብት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) እና አሜሪካ ወደ ሶማሊያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ቢልኩም በሶማሊያ እስካሁን አልተረጋጋችም፡፡ ኢትዮጵያም በአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ስር ወታደሮቿን ከላኩ ሀገራት በቀዳሚነት ትጠቀሳለች፡፡
በሶማሊያ በቅርቡ በተካደው ምርጫ ሰላማዊ የሚባል የስልጣን ሽግግር ተካሄደዷል፤ መሃመድ ፋርማጆ ስልጣናቸውን ለፕሬዝደንት ሐሰን ማሀሙድ አስረክበዋል፡፡