ከኢትዮጵያ ጋር ውዝግብ ውስጥ የገባችው ሶማሊያ ፕሬዝደንት ሀሰን ሸክ መሀሙድ አዲስ አበባ ገቡ
ፕሬዝደንቱ ወደ አዲስ አበባ የመጡት 34ኛውን የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ለመካፈል መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል
ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ባለው በፈረሙት የመግባቢያ ሰነድ ምክንያት ቁጣቸውን ያሰሙት የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሀሰን ሸክ መሀመድ አዲስ አበባ ገብተዋል
ከኢትዮጵያ ጋር ውዝግብ ውስጥ የገባችው ሶማሊያ ፕሬዝደንት ሀሰን ሸክ መሀሙድ አዲስ አበባ ገቡ።
ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ባለው የፈረንጆቹ ጥር አንድ ቀን በፈረሙት የመግባቢያ ሰነድ ምክንያት ቁጣቸውን ያሰሙት የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሀሰን ሸክ መሀመድ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዝደንቱ ወደ አዲስ አበባ የመጡት 37ኛውን የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ለመካፈል መሆኑን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሄ አብዲ የፈረሙት የመግባቢያ ሰነድ፣ ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና ሰጥታ በምላሹ 20 ኪሎሜትር ርዝመት ያለው የባህር ጠረፍ በ50 አመት የሊዝ ኪራይ እንድታገኝ የሚያስችል መሆኑ በወቅቱ ተገልጾ ነበር።
- ኢትዮጵያ ወደብ እንድትከራይ እና በምላሹ ለሶማሊላንድ እውቅና እንድትሰጥ ስምምነት ላይ መደረሱን ሶማሊላንድ አስታወቀች
- በስምምነቱ "የተጣሰ ሕግና የተሰበረ እምነትም የለም"- የኢትዮጵያ መንግስት
ነገርግን ሶማሊላንድን የራሷ ሉአላዊ ግዛት አካል አድርጋ የምታያት ሶማሊያ በስምምነቱ ከፍተኛ ቁጣ አሰማች፤ ከአምባሳደሯንም ከኢትዮጵያ ጠራች።
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ካቢኔያቸውን ሰብሰበው ሶማሊያ ስምምነቱ ሉአላዊነቷን የሚጥስ በመሆኑ እንደማትቀበለው ግልጽ አደረጉ።
ፕሬዝደንቱ በዚህ ሳያበቁ አጋርነት ለማግኘት ለበርካታ ሀገራት መሪዎች ስልክ በመደወል ከጎናቸው እንዲቆሙ ጥሪ አስተላልፈው ነበር።
ይህን የኘሬዝደንቱን ጥሪ ተከትል ግብጽ ሶማሊያ ሉአላዋነቷን ለማስጠበቅ የምታደርገውን ጥረት እንደምትደግፍ ግልጽ ማድረጓ ይታወሳል።
ከግብጽ በተጨማሪ የአረብ ሊግ፣ የአፍሪካ ህብረት፣ የአውሮፖ ህብረት እና ሌሎችም የሶማሊያ ሉአላዊ ድንበር ይጠበቅ የሚል መግለጫ በማውጣት ከሶማሊያ ጎን ቆሙ።
ፕሬዝደንት ሀሰን ሸክ መሀሙድ በስምምነቱ ዙሪያ ከአልጀዚራ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ከኢትዮጵያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ለማድረግ፣ ኢትዮጵያ ስምምነቱን መሰረዝ አለባት ሲሉም መናገራቸው ይታወሳል።
ፕሬዝደንቱ በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከህብረቱ ስብሰባ ጎን ለጎን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ተገናኝተው በጉዳዩ ላይ የመወያየት እቅድ ስለመያዛቸው አልታወቀም።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በቀረቡበት ወቅት ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር ግጭት ውስጥ የመግባት ፍላጎት የላትም ብለዋል።