ፖለቲካ
ሶማሊላንድ ከሶማሊያ ጋር ስለመዋሃድ ጉዳይ እንደማትወያይ ገለጸች
ሶማሊላንድ በፈረንጆቹ በ1991 ከሶማሊያ በይፋ መገንጠሏን ብታሳውቅም አለምአቀፍ ውቅና አላገኘችም
ከሶለማሊያ ጋር ለመዋሃድ እቅድ እንደሌላት የገለጸችው ሶማሊላንድ፣ የኡጋንዳው ፕሬዝደንት ሙሰቨኒ ከተናገሩት ጋር የሚቃረን መግለጫ አውጥታለች
ከሶለማሊያ ጋር ለመዋሃድ እቅድ እንደሌላት የገለጸችው ሶማሊላንድ፣ ውህደት እንዲፈጠር አደራድራለሁ ካሉት የኡጋንዳው ፕሬዝደንት ሙሰቨኒ ጋር የሚቃረን መግለጫ አውጥታለች።
ሙሰቨኒ የማደራደሩን ሚና እወጣለሁ ያሉት ባለፈው አርብ የሶማሊላንድ ልዩ መልእክተኛ ጃማ ሙሳ ጃማ በኡጋንዳ ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነበር።
ሶማሊላንድ በፈረንጆቹ በ1991 ከሶማሊያ በይፋ መገንጠሏን ብታሳውቅም አለምአቀፍ ውቅና አላገኘችም።
የሶማሊላንድ መንግስት ባወጣው መግለጫ "በሶማሊላንድ እና ሶማሊያ መካከል የሚደረግ ማንኛውም ንግግር በውህደት ጉዳይ አይደለም፣ ነገርግን ቀድሞ አንድ የሆነበሩት ሀገራት በተናጠል እንዴት ወደፊት መጓዝ አለባቸው በሚለው ላይ ነው" ብሏል።
ጎረቤቶቿ በእርስበእርስ ጦርነት ሲታመሱ ለላፉት ሶስት አስርት አመታት ሰላማዊ የሆነችው ሶማሊላንድ "በውህደት ጉዳይ ከሶማሊያ ጋር የመወያየት እቅድ እንደሌላት" ገልጻለች።
ሶማሊላንድ ከሶማሊያ በምትዋሰንበት አወዛጋቢ ቦታዎች ያሉ የጎሳ መሪዎች የሶማሊያዋ ራስ ገዝ ፑንትላንድ አካል መሆን ይፈልጋሉ።
በዚህም ምክንያት በሶማሊላንድ ጦር እና በአካባቢው ሚሊሻዎች መካከል ግጭት ይስተዋላል።