ሶማሊ ላንድ ከ16 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፓርላማ ምርጫ አካሄደች
በምርጫው ላይ ድምጽ ለመስጠትም በሀገሪቱ ከሚገኙ 4 ሚሊየን ሰዎች 1 ሚሊየን ሰዎች ተመዝግበዋል
82 መቀመጫ ላለው የሶማሊ ላንድ ፓርላማ ሶስት የፖለቲካ ፓርቲዎች 246 እጩዎችን አቅርበዋል
ሶማሊ ላንድ በፈረንጆች ከ2005 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የፓርላማ ምርጫ ማካሄዷ ተነግሯል።
እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ1991 ከሶማሊያ ጋር የተለያየቸው ሶማሊ ላንድ በትናትናው እለት ነው የፓርላማ ምርጫ ያካሄደችው።
ሶማሊ ላንድ ፕሬዚዳንት ሙሲ ቢሂ ወደ ምርጫ ጣቢያ በማቅናት ድምጽ ከሰጡ በኋላ "ሰላማዊ ምርጫ" ሲሉ አስተያየት መስጠታቸው ተሰምቷል።
82 መቀመጫ ላለው የሶማሊ ላንድ ፓርላማ ሶስት የፖለቲካ ፓርቲዎች 246 እጩዎችን አቅርበዋል።
በምርጫው ላይ ድምጽ ለመስጠትም በሀገሪቱ ከሚገኙ 4 ሚሊየን ሰዎች 1 ሚሊየን ያህሉ መመዝገባቸውንም የሶማሊ ላንድ ብሄራው ምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል።
የሶማሊ ላንድ የፓርላማ ምርጫ ከብሄራው ምርጫ ኮሚሽኑ ጋር በተያያዘ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በነበረ አለመግባባት ከ10 ዓመት በላይ መዘግየቱ ይታወቃል።
በመጨረሻም የፖለቲካ ሀይሎቹ በምርጫ ኮሚሽኑ ላይ ነመስማማታቸው ነው ምርጫው በትናትናው እለት የተካሄደው።
እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ1991 ከሶማሊያ ጋር ተለያየቸው ሶማሊ ላንድ እስካሁን እንደ ሀገር ከዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እውቅና አላገኘችም።
ሶማሊ ላንድ ያለፉትን 30 ዓመታት በእር በእርስ ጦርነት ካሳለፉት ሌሎች የሶማሊያ ክፍል ጋር ስትነጻጸር ሰላማዊ ሀገር ነች።