በ40 የምርጫ ክልሎች ላይ ሰኔ 14 ድምጽ እንደማይሰጥ ቦርዱ ገለፀ
በጸጥታ እና በመራጮች ምዝገባ አቤቱታ ምክንያት ነው በ40 የምርጫ ክልሎች ድምጽ የማይሰጠው
ድምጽ የማይሰጥባቸው ስፍራዎች በ 6 ተለያዩ ክልሎች ውስጥ የሚገኙ ናቸው
በተለያዩ ምክንያቶች (በጸጥታ እና በመራጮች ምዝገባ አቤቱታ) ድምጽ መስጠት ሂደቱ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ተግባራዊ ሊሆን የማይችልባቸው የምርጫ ክልሎችን ቦርዱ ይፋ አድርጓል፡፡ እነርሱም የሚከተሉት የምርጫ ክልሎች ናቸው፡-
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል (4 ምርጫ ክልል)
የመራጮች ምዝገባ ያልተጀመባቸው ቦታዎች
1. መተከል ምርጫ ክልል
2. ሺናሻ ልዩ ምርጫ ክልል
3. ካማሽ ምርጫ ክልል
4. ዳለቲ ምርጫ ክልል
ሶማሌ ክልል (14 ምርጫ ክልል)
የመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ አቤቱታ የቀረበባቸው እና የማጣራት ሂደቱ ላይ የሚወሰኑ
1. አራቢ የምርጫ ክልል
2. ደግሃመዶ ምርጫ ክልል
3. ጎዴ የምርጫ ክልል
4. ጂግጂጋ 1 የምርጫ ክልል
5. ጂግጂጋ 2 የምርጫ ክልል
6. ቀብሪደሃር ምርጫ ክልል
7. ቀላፎ ምርጫ ክልል
8. ዋርዴር ምርጫ ክልል
9. ፊቅ ምርጫ ክልል
10. ገላዲን ምርጫ ክልል
11. ደገሃቡር ምርጫ ክልል
የመራጮች ምዝገባ ሂደት በክልሉ መስተዳድር የተቋረጠባቸው
1. አይሻ ምርጫ ክልል
2. ኤረር ምርጫ ክልል
3. ሽንሌ ምርጫ ክልል
ኦሮሚያ ክልል (7 ምርጫ ክልል)
የመራጮች ምዝገባ ያልተጀመረባቸው ( በጸጥታ ችግር)
1. ቤጊ ምርጫ ክልል - ምእራብ ወለጋ
2. ሰኞ ገበያ ምርጫ ክልል - ምእራብ ወለጋ
3. አያና ምርጫ ክልል - ምስራቅ ወለጋ
4. ገሊላ ምርጫ - ምስራቅ ወለጋ
5. አሊቦ ምርጫ ክልል -ሆሮ ጉድሩ
6. ጊዳም ምርጫ ክልል- ሆሮ ጉድሩ
7. ኮምቦልቻ ምርጫ ክልል- ሆሮ ጉድሩ
አማራ ክልል (8 ምርጫ ክልል)
የመራጮች ምዝገባ ያልተጀመረባቸው (በጸጥታ ችግር)
1. ማጀቴ (ማኮይ) ምርጫ ክልል
2. አርጎባ ልዩ ምርጫ ክልል
3. ሸዋሮቢት ምርጫ ክልል
4. ኤፌሶን ምርጫ ክልል
5. ጭልጋ 1 ምርጫ ክልል
6. ጭልጋ 2 ምርጫ ክልል
7. ላይ አርማጭሆ ምርጫ ክልል
8. ድልይብዛ ምርጫ ክልል
ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል (4 ምርጫ ክልል)
የመራጮች ምዝገባ ያልተጀመረባቸው (በጸጥታ ችግር)
1. ዘልማም ምርጫ ክልል
2. ሱርማ ልዩ ምርጫ ክልል
3. ዲዚ ልዩ ምርጫ ክልል
4. ሙርሲ ልዩ ምርጫ ክልል
ሐረሪ ክልል (3 ምርጫ ክልል)
የመራጮች ምዝገባ ከፍተኛ የተዛባ አሰራር የታየባቸው እንዲሁም በህግ የተያዘ ጉዳይ
1. ጀጎል ልዩ ምርጫ ክልል
2. ጀጎል መደበኛ ምርጫ ክልል
3. ጀጎል ዙሪያ እና ሁንደኔ ምርጫ ክልል
ልዩ መግለጫ
በጋምቤላ ክልል ዲማ ምርጫ ክልል እና አኮቦ ምርጫ ክልል ከፍተኛ የመሰረተ ልማት እና የመጓጓዥ ችግር በመኖሩ በልዩ ሁኔታ የክልል እና የፌደራል መንግስትን ከፍተኛ እገዛ ይጠይቃል ብሏል ቦርዱ።