ቦርዱ ለዓለም አቀፍ ሪፕብሊካን ኢንስቲቲዩት እና ዓለም አቀፍ የዴሞክራቲክ ኢንስቲቲዮት ነው እውቅና የሰጠው
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሁለት ዓለም አቀፍ ተቋማት የምርጫ መታዘብ እውቅና መስተቱን አስታወቀ።
ቦርዱ በዛሬው እለት እንዳስታወቀው ምርጨውን የመታዘብ እውቅናው ለዓለም አቀፍ ሪፕብሊካን ኢንስቲቲዩት እና ለዓለም አቀፍ የዴሞክራቲክ ኢንስቲቲዮት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ነው የሰጠው።
ቦርዱ የድርጅቶቹ የጋራ የታዛቢ ቡድን ያቀረበውን የጥናት ዘዴ በማየት እንዲሁም በዓለም አቀፍ ታዛቢዎች መሰረታዊ መርሆዎች እና የታዛቢዎች ዓለም አቀፍ የስነ-ምግባር ደንብን በተከተለ መልኩ እንደሚሰሩ ስምምነት ላይ በመድረስ የመታዘብ እውቅናውን ፣ መስጠቱንም አስታውቋል።
በዓለም አቀፉ የኮቪድ ወረርሽኝ የተነሳ የታዛቢ ቡድኑ የመታዘብ ተግባር የሚያከናውንበት የቦታ ስፋት ውስንነት እንደሚኖረውና ይህንንም በሚያደርጋቸው ስራዎች እና ማጠቃለያዎች ላይ የሚገለጽ መሆኑን ታዛቢ ቡድኑ እና ቦርዱ በጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውንም አስታውቋል።
ቦርዱ ከዚህ በፊት ለ45 የአገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች እውቅና መስጠቱ ይታወሳል።