የኡጋንዳ ጦር አዛዥ ሆነው የተሾሙት የሙሴቬኒ ልጅ በሙሰኞች ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ሲሉ ዛቱ
ኡጋንዳን ለ38 አመት ያስተዳደሩት ሙሴቬኒ ልጃቸውን የሀገሪቱ ዋና ጦር አዛዥ አድርገው የሾሙት ባለፈው ሳምንት ነበር
ኡጋንዳን ለ38 አመት ያስተዳደሩት የ79 አመቱ ሙሴቬኒ የ40 አመት ልዳቸውን ሙሆዚ ኬነሩጋባን የሀገሪቱ ዋና ጦር አዛዥ አድርገው የሾሙት ባለፈው ሳምንት ነበር
የኡጋንዳ ጦር አዛዥ ሆነው የተሾሙት የፕሬዝደንት ሙሴቬኒ ልጅ በጦሩ ውስጥ ባሉ ሙሰኞች ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ሲሉ ዛቱ።
የኡጋንዳ ጦር አዛዥ የሆኑት የፕሬዝደንት ዩሪ ሙሴቬኒ ልጅ በጦሩ ውስጥ ባለው የሙስና ተግባር ላይ እርምጃ እወሰዳሉ ሲሉ ዛቻ አሰምተዋል።
ኡጋንዳን ለ38 አመት ያስተዳደሩት የ79 አመቱ ሙሴቬኒ የ40 አመት ልጃቸውን ሙሆዚ ኬነሩጋባን የሀገሪቱ ዋና ጦር አዛዥ አድርገው የሾሙት ባለፈው ሳምንት ነበር።
በትናንትናው እለት በተካሄደ ይፋዊ የርክክብ ስነስርአት ላይ ኬነሩጋባ ሙስናን በመዋጋት የወታደሮችን ኑሮ እንደሚያሻሽሉ እና የሀብት ብክነትን እንደሚቀንሱ ቃል መግባታቸውን የመከላከያ ሚኒስቴሩ ያወጣው የጦሩ መግለጫ ገልጿል።
የኡጋንዳ ጦር በሶማሊያ እና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሰላም አስከባሪ ሆኖ በመዝመት ከእሰላማዊ ታጣቂዎች ጋር በሚደረገው ውጊያ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።
የኡጋንዳ ተቃዋሚዎች ሙሴቬኒ ልጃቸውን በቂ ልምድ ሳይኖረው የፖለቲካ ስልጣን እንዲይዝ እያመቻቹ ነው የሚል ክስ ያቀርባሉ። ሙሴቬኔ ግን ልጃቸውን ለፕሬዝደንትነት አስባዋል የሚለውን ክስ አስተባብዋል።
በ2022 ኬነሩጋባ ኤክስ (በቀድሞው ቲዊተር) ገጹ ጎረቤት ሀገር ኬንያን እወራለሁ ብሎ መዛታቸውን ተከትሎ ሙሴቬኒ ከምድር ጦር አዛዥነት አንስተዋቸው ነበር።
በዩክሬን ላይ "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" የከፈቱትን የሩሲያውን ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲንን ያደነቀው ኬነሩጋባ ቆየት ብሎ ዛቻውን ቀልድ ነው ማለቱ ይታወሳል።