ደቡብ አፍሪካ አለምአቀፉ ፍርድ ቤት የእስራኤልን የራፋ ጥቃት እቅድ እንዲመረምረው ጠየቀች
ጋዛን ሲያስተዳድር ከነበረው ሀማስ ጋረ እየተዋጋች ያለችው እስራኤል ግን የቀረበባትን የዘር ማጥፋት ክስ አልተቀበለችውም
መቀመጫው ሄግ ያደረገው ፍርድ ቤቱ በኤክስ ገጹ ላይ ደቡብ አፍሪካ ያቀረበችውን ጥያቄ መቀበሉን አረጋግጧል
ደቡብ አፍሪካ አለምአቀፉ ፍርድ ቤት የእስራኤልን የራፋ ጥቃት እቅድ እንዲመረምረው ጠየቀች።
ደቡብ አፍሪካ የእስራኤል ራፋን የማጥቃት እቅድ ንጹሃንን ለመከላከል ተጨማሪ አስቸኳይ እርምጃዎች ያስፈልጉት እንደሆነ እንዲመረምረው መጠየቋን በትናንትናው እለት አስታውቃለች።
ደቡብ አፍሪካ በእሰራኤል ላይ ያቀረበችውን ክስ የተመለከተው አለምአቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት (አይሲጄ) እስራኤል ጦሯ በፍልስጤማውያን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዳይፈጽም እንድታደርግ ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር።
ጋዛን ሲያስተዳድር ከነበረው ሀማስ ጋረ እየተዋጋች ያለችው እስራኤል ግን የቀረበባትን የዘር ማጥፋት ክስ አልተቀበለችውም።
በተለያዩ የጋዛ አካባቢዎች የተደረጉ ጦርነቶችን የሸሹ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች የሚገኙባትን በግብጽ ድንበር የምትገኘውን ራፋን ለማጥቃት እቅድ አውጥታለች።
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ የደቡብ አፍሪካ መንግስት እስራኤል በራፋ አደርገዋለሁ ያለችው ወታደራዊ ጥቃት የከፍ ግድያ እና ውድመት የሚያስከትል በመሆኑ በእጅጉ እንደሚያሳስበው ለፍርድ ቤቱ ባስገባው ጥያቄ ጠቅሷል።
"ይህ የዘር ማጥፋት ህግን እና ፍርድ ቤቱ ጥር 26 ያስተላለፈውን ውስኔ የሚጥስ ነው"
መቀመጫው ሄግ ያደረገው ፍርድ ቤቱ በኤክስ ገጹ ላይ ደቡብ አፍሪካ ያቀረበችውን ጥያቄ መቀበሉን አረጋግጧል። ነገርግን ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ መቼ ውሳኔ እንደሚሰጥበት አልገለጸም።
ከዚህ በፊት በነበሩ አሰራሮች ፍርድ ቤቱ መሬት ያሉ ሁኔታዎች ሲቀሩ ተጨማሪ አስቸኳይ እርምጃዎችኝ የሚወስድበት አሰራር አለው።
የእስራኤን ራፋን የማጥቃት እቅድ የግጭቱ አደራዳሪዎች እና ግብጽ ተቃውመውታል።
በተለይም ግብጽ እስራኤል በራፋ ጥቃት የምትከፍት ከሆነ ከእስራኤል ጋር ከ40 አመታት በፊት በካምፕ ዴቪድ የፈረመችውን የሰላም ስምምነት ልትሰርዘው እንደምትችል አስፈራርታለች።