በአፍጋኒስታን የነበሩ የውጭ ዜጎችን የማስወጣት ቀነ ገደብ ከሶስት ቀን በፊት መጠናቀቁ ይታወሳል
ደቡብ አፍሪካ 35 ዜጎቿን ከአፍጋኒስታን ማስወጣቷን ገለጸች።
የሀገሪቱ ዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ቢሮ እንዳስታወቀው በአፍጋኒስታን የነበሩ 35 ዜጎችን ማስወጣት ተችሏል።
ይሁንና አሁንም አንድ ደቡብ አፍሪካዊ በካቡል ከተማ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን እስከመቼ በዛው እንደሚቆይ አልተገለጸም።
እነዚህ ግለሰቦች ከአፍጋኒስታን እንዲወጡ የተደረገው በተለያዩ መንገዶች ዜጎቹ ካቡልን ለቀው እንዲወጡ መንግስት ድጋፍ ማድረጉን የሲጂቲኤን አፍሪካ ዘገባ ያስረዳል።
የደቡብ አፍሪካ መንግስት አሁንም ያልተመዘገቡ ዜጎች በአፍጋኒስታን ሊኖሩ እንደሚችሉ ገልጾ የቀሩ ዜጎ በኢስላማባድ በሚገኘው የአገሪቱ ኢምባሲ ወይም በፕሪቶሪያ መመዝገብ እንደሚቻል ቢሮው ጥሪ አቅርቧል።