ጃኮብ ዙማ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲመለሱ የደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤት አዘዘ
አመጽ ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል በጤና ሰበብ ከእስር ቤት መውጣታቸውንም ፍርድ ቤቱ ተቃውሟል
ፍርድ ቤቱ በጤና እክል ሰበብ ከማረሚያ ቤት ወጥተው በቤታቸው እንዲቆዩ መደረጉ ህጋዊ አይደለም ብሏል
የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀድሞው የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ አዘዘ፡፡
ፍርድ ቤቱ የጤና እክል ገጥሟቸዋል በሚል ዙማ ከማረሚያ ቤት ወጥተው ያለፉትን ሶስት ወራት በመኖሪያ ቤታቸው ማሳለፋቸውን ተቃውሟል፡፡
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት በኮሮና ቫይረስ ተያዙ
በቀድሞው የሃገሪቱ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽነር ተላልፎ የነበረውን ውሳኔው በመሻርም ነው ዙማ ተመልሰው ወደ ማረሚያ ቤት እንዲገቡና እንዲታሰሩ ያዘዘው፡፡
ስልጣንን አላግባብ በመጠቀምና በሙስና ተከሰው ፍርድ ቤት በመመላለስ ላይ ያሉት ጃኮብ ዙማ ችሎት ተዳፈሩ በሚል ባሳለፍነው ሃምሌ በሃገሪቱ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት የ15 ወራት እስር እንደተላለፈባቸው ይታወሳል፡፡
“አፍሪካ በተመድ ጸጥታው ም/ቤት ቋሚ መቀመጫ አለማግኘቷ አሳዛኝ ነው” የደቡብ አፍሪካ እና ሴኔጋል መሪዎች
ሆኖም የጤና እክል ገጥሟቸዋል በሚል ያለፉትን ሶስት ወራት ከማረሚያ ቤት ወጥተው በመኖሪያ ቤታቸው ነው ያሳለፉት፡፡ ይህ በቀድሞው የሃገሪቱ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽነር አርተር ፍሬዘር ውሳኔ የሆነ ነው፡፡
ኮሚሽነር አርተር፤ ዙማ እስር ላይ ሳሉ አንድ ነገር ቢገጥማቸው ልክ እንደካሁን ቀደሙ ሁሉ ከፍተኛ አመጽ ሊቀሰቀስ ይችላል በሚል ነበር ከማረሚያ ቤት እንዲወጡ ያደረጉት፡፡ ይህንንም የተለያዩ የሃገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበውታል፡፡
ትዕዛዙ ህጋዊ እንዳይደለ የገለጸው ፍርድ ቤቱ ግን “አመጽና ግርግሮች አንድን ወንጀለኛ ለመፍታት በቂ ምክንያት አይደሉም” በሚል ትዕዛዙን በመቀልበስ ዙማ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲመለሱ ወስኗል፡፡
የዙማ ደጋፊዎች ውሳኔውን ተቃውመዋል፡፡ የቀድሞውን ርዕሰ ብሔር ወደ እስር ከየትኛውም እርምጃ እንጠብቃለን በሚልም ዝተዋል፡፡
ይህ ልክ እንደ ከአሁን ቀደሙ ሁሉ ሁካታ እና ግርግርን ይፈጥር ይሆን በሚል በብዎች ዘንድ ስጋትን ፈጥሯል፡፡
ደጋፊዎቹ የእስር ውሳኔው በተላለፈበት ጊዜ በቀሰቀሱት አመጽ የ400 ገደማ ሰዎች ህይወት ማለፉ እና የኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የሌሎች ሃገራት ዜጎች ንብረት በከፍተኛ ሁኔታ መዘረፉ ይታወሳል፡፡