የቻይናው ዲፕሲክ "ብዙ መጠን" ያለው የግለሰብ መረጃ እየሰበሰበ ነው ተባለ
የሀገሪቱ ብሔራዊ የስለላ አገልግሎት የመንግስት ድርጅቶች ከዲፕሲክ መተግበሪያ እንዲጠነቀቁ ባለፈው ሳምንት ማስታወሻ መላኩን አስታውቋል
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/10/243-143307-img-20250210-132956-702_700x400.jpg)
ቤጂንግ የትኛውም ኩባንያ መረጃ እንዲሰበስብላት ወይም ህግ ጥሶ መረጃ እንዲያከማችላት በፍጹም አልጠየቀችም ብላለች
የቻይናው ዲፕሲክ "ብዙ መጠን" ያለው የግለሰብ መረጃ እየሰበሰበ ነው ተባለ።
የደቡብ ኮሪያ የስለላ ኤጀንሲ የቻይናው የአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ(ኤአይ) መተግበሪያ "ብዙ መጠን" ያለው የግለሰቦች መረጃ እየሰበሰበና ራሱን ለማሰልጠን እየተጠቀመበት ነው ሲል ከሰሰ።
ከስድስት ሚሊዮን ዶላር ባልበለጠ ገንዘብ የበለጸገው ዲፕሲክ በዘርፉ ብዙ ርቀት ሄደናል የሚሉትን ምዕራባውያን ራሳቸውን እንዲገመግሙ አድርጓቸዋል።
የሀገሪቱ ብሔራዊ የስለላ አገልግሎት(ኒስ) የመንግስት ድርጅቶች ከዲፕሲክ መተግበሪያ እንዲጠነቀቁ ባለፈው ሳምንት ማስታወሻ መላኩን አስታውቋል።
ከሌሎች መረጃ ሰብሳቢ የኤአይ አገልግሎቶች በተቃራኒ ዲፕሲክ የግልሰቦችን መረጃ ልውውጥ በሚጻጻፉበት ወቅት በመመዝገብ ቻይና ላለው ሰርቨር እንደሚልክ ኒስ በዛሬው እለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የተወሰኑ የደቡብ ኮሪያ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የደህንነት ስጋትን በምክንያትነት በመጥቀስ መተግበሪያውን አግደዋል። ቀደም ሲል አውስትራሊያና ታይዋን መተግበሪያው እግድ እንዲጣልበት አስጠንቅቀው ነበር።
ኒስ እንደገለጸው ዲፕሲክ ምርት አስተዋዋቂዎች የተጠቃሚዎች መረጃ ያለገደብ እንዲያገኙና የደቡብ ኮሪያ ተጠቃሚዎችን መረጃ ቻይና ውስጥ በሚገኘው ሰርቨሩ ማከማቸቱን ገልጿል።
ኤጀንሲው እንደገለጸው በቻይና ህግ መሰረት የቻይና መንግስት እንዲህ አይነት መረጃዎችን ጠይቆ ማግኘት ይችላል።
ዲፕሴክ በተለያዩ ቋንቋዎች ለቀረቡለት ጥያቄዎች የተለያዩ መልሶች እንደሚሰጥ ኒስ አስታውሷል።
ደቡብ ኮሪያ በዲፕሲክ ላይ ስለወሰደችው እርምጃ የተጠየቁት የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የቻይና መንግስት ለመረጃ ሚስጥራዊነትና ደህንነት ትልቅ ቦታ እንደሚሰጥና በህጉ መሰረት እንደሚጠብቅ ተናግረዋል።
ቃል አቀባይዋ ቤጂንግ የትኛውም ኩባንያ መረጃ እንዲሰበስብላት ወይም ህግ ጥሶ መረጃ እንዲያከማችላት በፍጹም አልጠየቀችም ብለዋል።