ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ ንግግር ለመጀመር አጥጋቢ እቅድ እንዳልደረሳት ገለጸች
ፕሬዝደንት ትራምፕና የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን አድርገውታል ስለተባለው ንግግር በዋሽንግተንና በሞስኮ በኩል እረስበእርሳቸው የሚቃረኑ መልእክቶች እየተላለፉ ናቸው
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/10/243-123448-ba4113b793b06a8d055656da088dde76_700x400.jpeg)
ፑቲን ከሁለት ሳምንት በኋላ ሶስት አመት የሚሞላውን ጦርነት የሩሲያ ህልውና ጉዳይ አድርጠው ይቆጥሩታል
ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ ንግግር ለመጀመር አጥጋቢ እቅድ እንዳልደረሳት ገለጸች።
ሞስኮ በዩክሬን ጉዳይ ንግግር ለመጀመር አጥጋቢ እቅድ እንዳልደረሳት የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሚካኤል ጋሉዚን ይህን ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ፑቲን ዋሽንግተን በዩክሬን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ለማስቆም የሚደረጉ ንግግሮች መሻሻል አሳይተዋል ማለታቸውን ተከትሎ ነው።
"ንግግሮች የሩሲያን ተገቢ ጥያቄዎች ከግምት በማስገባትና የቀውሱን ትክክለኛ መነሻ በሚፈቱ መልኩ በተግባራዊ እርምጃዎች መደገፍ አለባቸው" ሲሉ ጋሉዚን ለሩሲያው ሪያ የዜና አገልግሎት መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
"አንዲህ አይነት ተጨባጭ የንግግር እቅዶች አልተቀበልንም"ብለዋል ጋሉዝኒ።
ፕሬዝደንት ትራምፕና የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ሶስት አመት ገደማ ያስቆጠረውን የዩክሬን ጦርነት በማስቆም ጉዳይ ያደርጉታል ስለተባለው ንግግር በዋሽንግተንና በሞስኮ በኩል እረስበእርሳቸው የሚቃረኑ መልእክቶች እየተላለፉ ናቸው።
ትራምፕ በሳምንቱ መጨረሻ ከፑቲን ጋር መነጋገራቸውን ገልጸው፣ ተጨማሪ ውይይቶች እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
"መሻሻሎች አሳይተናል ብዬ አምናለሁ" ያሉት ትራምፕ "የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት እንዲቆም እንፈልጋለን" ብለዋል።
የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ በፑቲንና በትራምፕ ንግግር መካከል የተለያዩ መልእክቶች እየወጡ መሆናቸውንና እሳቸው እያንዳንዱን ነገር እንደሚያውቁ ገልጸዋል።
"ስለዚህ አግባብ ሁሉንም ላረጋጋግጥ ወይም ላስተባብል አልችልም" ብለዋል።
ትራምፕ በዩክሬን እየተካሄደ የሚገኘው ጦርነት እንዲቆም እንደሚፈልጉና በጉዳዩ ላይ ከፑቲን ጋር ተገናኝተው እንደሚመክሩ በተደጋጋሚ ተናግረዋል። ባለፈው እሁድ እለት ትራምፕ በተገቢው ጊዜ ፑቲንን እደሚያገኟቸው ገልጸዋል።
ፑቲን ከሁለት ሳምንት በኋላ ሶስት አመት የሚሞላውን ጦርነት የሩሲያ ህልውና ጉዳይ አድርጠው ይቆጥሩታል። ዩክሬንና ምዕራባውያን አጋሮቿ ደግሞ የቅኝ ግዛት አይነት የመሬት ነጠቃ አድርገው ይመለከቱታል።