ደቡብ ኮሪያ በኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ አውዳሚ እሳት አደጋ መከሰቱን ተከትሎ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራች
ማርቸዲስ ቤንዝ መኪና ላይ በደረሰ እሳት አደጋ ምክንያት ከ140 በላይ ሌሎች መኪኖች በእሳት ወድመዋል
ሀገሪቱ በኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ በሚገጠሙ ባትሪዎች ዙሪያ አዲስ ህግ ልታወጣ እንደምትችል አስታውቃለች
ደቡብ ኮሪያ በኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ አውዳሚ እሳት አደጋ መከሰቱን ተከትሎ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራች፡፡
በሳለፍነው ሳምንት በሀገሪቱ መዲና ሴኡል ባለ አንድ ጋራጅ ውስጥ የነበረ ማርቸዲስ ቤንዝ ኮሪያ ግሩፕ ሰራሽ ምርት ላይ በተነሳ እሳት 140 ተሸከርካሪዎች እንዲወድሙ ምክንያት ሆኗል፡፡
ይህ ተከትሎ የሀገሪቱ ዋነኛ ተቋማት በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ላይ በሚገጠሙ ባትሪዎች ዙሪያ አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጠዋል፡፡
የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሃላፊዎችን ጨምሮ ሌሎች ተቋማት እና ባለሙያዎች በተካፈሉበት በዚህ ስብሰባ ዋናው ምክንያት በተደጋጋሚ በሀገሪቱ የሚያጋጥሙ የኤሌክትሪክ ባትሪዎች ዙሪያ አዲ ህግ እንደሚያወጣ ይጠበቃል፡፡
የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪን በአራት ደቂቃ የሚሞላ ቻርጀር ተሰራ
በዚህ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ በደቡብ ኮሪያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያዎች ሁሉ በመሳተፍ ላይ እንደሆኑ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
መሰረታቸውን ደቡብ ከሮያ ያደረጉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያዎች የሚጠቀሟቸውን ባትሪዎች አስቀድመው እንዲያስመዘግቡ ሊደረግ እንደሚችል በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ከአንድ ወር በፊት ኪያ ኩባንያ ሰራሽ የሆነ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ተመሳሳይ የእሳት አደጋ አጋጥሞ ነበር ተብሏል፡፡
በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ለይ የሚደርሱ እሳት አደጋዎች በቶሎ ማወቅ እና አደጋው ከተከሰተ ደግሞ በቀላሉ ለመቆጣጠር አደጋች እንደሆኑ የዘርፉ ባለሙያዎች በመናገር ላይ ናቸው፡፡
በደቡብ ኮሪያ ከፈረንጆቹ 2013 እስከ 2022 ድረስ 1 ሺህ 399 የእሳት አደጋዎች በጋራጆች ውስጥ ተከስተዋል ተብሏል፡፡