ደቡብ ኮሪያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ወደ ፒዮንግያንግ እንደሚልክ ዛተች
ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዮል በዓመቱ ውስጥ ትናንሽና ድብቅ አውሮፕላኖች እንዲመረቱ ትዕዛዝ ሰጥተዋል ተብሏል
ሰላይ ናቸው የተባሉ የሰሜን ኮሪያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በተደጋጋሚ ሴኡል መግባታቸው በኮሪያ ሰርጥ ውጥረቱን አባብሶታል
ደቡብ ኮሪያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ወደ ፒዮንግያንግ እንደሚልክ ዛተች
ፒዮንግያንግ ተጨማሪ ሰው አልባ አውሮፕላን ወደ ደቡብ ከላከች ሴኡል አጻፋውን እመልሳለሁ ብላለች።
የፕሬዚዳንት ዩን ጽ/ቤት ከፍተኛ ባለስልጣን ለጁንግአንግ ኢልቦ እንደተናገሩት ሀገራቸው ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ወደ ሰሜን ኮሪያ በመላክ ትከላከላለች።
“ሰሜኖች ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ወደ ደቡብ ኮሪያ ከላኩ እኛ እነሱን በጥይት በመተኮስ ዝም ብለን ምላሽ አንሰጥም። እንደ ምላሹ አካል ሴኡል የራሷን ሰው አልባ አውሮፕላኖች በተመጣጣኝ መርህ መሰረት ወደ ሰሜን ኮሪያ ትልካለች" ብለዋል።
"እስከ ፒዮንግያንግ እና የሚሳይል ማስወንጨፊያ እስከሆነው ቶንግቻንግ ጣቢያ ድረስ ልንልክ እንችላለን" ሲሉ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።
ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዮል በደቡብ ኮሪያ የጦር ኃይሎች ስር ያለ ሰው አልባ አውሮፕላን ቡድን እንዲቋቋም እና በዓመቱ ውስጥ ትናንሽ ድብቅ አውሮፕላኖች እንዲመረቱ ትዕዛዝ ሰጥተዋል ተብሏል።
ካለፈው ወር የድሮን ወረራ በኋላ ፕሬዝዳንት ዮል ወደ ደቡብ ለሚገባ እያንዳንዱ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ሁለት ወይም ሦስት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ወደ ሰሜን እንዲላክ አዘዋል ነው የተባለው።
ሰላይ ናቸው የተባሉ የሰሜን ኮሪያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ካለፈው ወር ጀምሮ በተደጋጋሚ ወደ ሴኡል መግባታቸው የኮሪያን ሰርጥ ውጥረት አባብሶታል።