የደቡብ ኮሪያ ቀዳማዊ እመቤት ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑ ተገለጸ
ቅሌቱ ፕሬዝደንት ዩን ሱክ ዮኦል ፓርቲያቸው በሚያዝያ ወር በተካሄደው ምርጫ እንዲሸነፍ አሉታዊ አስተዋጽኦ አድርጓል
ቀዳማዊ እመቤት ኪም ኪዮን ሂ በስቶክ ማጭበርበር እና 2,200 ዶላር ዋጋ ባለው የቅንጦት ቦርሳ ጉዳይ በሙስና ተጠርጥረው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አቃቤ ህግ አስታውቋል
የደቡብ ኮሪያ ቀዳማዊ እመቤት በማጭበርበር ተጠርጥረው እየተመረመሩ መሆኑ ተገለጸ።
የደቡብ ኮሪያ ቀዳማዊ እመቤት ኪም ኪዮን ሂ በስቶክ ማጭበርበር እና 2,200 ዶላር ዋጋ ባለው የቅንጦት ቦርሳ ጉዳይ በሙስና ተጠርጥረው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አቃቤ ህግ አስታውቋል።
ይህ ምርመራ እየተካሄደ ያለው ተቃዋሚዎች የመንግስት የስነ ምግባር መመሪያ በመጣስ ቅንጡ የዳዮር ቦርሳ የተቀበሉት እና በስቶክ ማጭበርበር ውስጥ ሚና እንዳላቸው በሚጠረጠሩት ቀዳሚዊ እመቤት ላይ ልዩ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ እያደረጉ ባለበት ወቅት ነው።
የሴኡል ማዕከላዊ ግዛት የአቃቤ ህግ ቢሮ ባወጣው መግለጫ አቃ ህግ ባለፈው ቅዳሜ በኪም ላይ "የፋት ለፊት ጥያቄ" ማድረጉን ገልጿል።
ባለፈው አመት በድብቅ ካሜራ የተቀረጸ ቪዲዮ ኪም 2,200 ዶላር ዋጋ ያለው ቅንጡ ቦርሳ ሲቀበሉ ታይተዋል። የሀገሪቱ ጋዜጦች ይህን ክስተት 'የዳዮር ባግ ስካንዳል' ወይም የዳዮር ቦርሳ ቅሌት ሲሉ ጠርተውት ነበር።
ቅሌቱ ፕሬዝደንት ዩን ሱክ ዮኦል ፓርቲያቸው በሚያዝያ ወር በተካሄደው ምርጫ እንዲሸነፍ አሉታዊ ተጽዕኖ አድርጓል። ይህ ቀዳማዊ እመቤቷ የተቀበሉት ስጦታ፣ ማንኛውም የደቡብ ኮሪያ መንግስት ባለስልጣናት እና ሚስቶቻቸው ከ750 በላይ ዶላር ዋጋ ያላቸውን ስጦታቸው እንዳይቀበሉ የሚከለክለውን ህግ የሚጥስ ነው።
የኪም ረዳቶች ለመርማሪዎች እንደተናገሩት ቀዳማዊ እመቤቷ ቦርሳውን በገዙበት ቀን እንድትመልስ ቢነገራትም፣ ረስተው አለመመለሳቸውን ሮይተርስ ዮንሀፕ ዜና አገልግሎትን ጠቅሶ ዘግቧል።
ዩን የቦርሳውን ቅሌት በተመለከተ በየካቲት ወር ባደረጉት የመጀመሪ ንግግር ጉዳዩ ፓለቲካዊ ወጥመድ ነው አጣጥለውት ነበር። ዩን እንዳሉት ባለቤታቸው ኪም ስጦታው የተቀበሉት አልቀበልም ለማለት አስቸጋሪ ስለሆነቸባቸው ነው ነበር ያሉት።
ነገርግን ዩን ዘግየት ብለው በግንቦት በሰጡት መግለጫ የባለቤታቸው ስጦታ መቀበል ተገቢ አለመሆኑን በመግለጽ ይቅርታ ጠይቀዋል።