ብሔራዊ የግዳጅ ውትድርና አገልግሎት ላለመስጠት በሚል ሆን ብሎ ክብደት የጨመረው ሰው
ደቡብ ኮሪያ እያንዳንዱ ዜጋ ለ18 ወራት ሀገሩን በውትድርና የማገልገል ግዴታን ጥላለች
ግለሰቡ በክብደቱ መጨመር ምክንያት ለወታደራዊ ግዳጅ ጦሩን ባይቀላቀልም ማህበራዊ አገልግሎቶችን እንዲሰጥ ተፈርዶበታል
ብሔራዊ የግዳጅ ውትድርና አገልግሎት ላለመስጠት በሚል ሆን ብሎ ክብደት የጨመረው ሰው
እስያዊቷ ደቡብ ኮሪያ እድሜያቸው 18 ዓመት እና ከዛ በላይ የሆኑ ዜጎቿ ቢያንስ ለ18 ወራት የውትድርና አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድድ ህግ አላት።
ስሙ ያልተጠቀሰው አንድ የሀገሪቱ ዜጋም ይህን የግዴታ አገልግሎት ላለመስጠት ሲል የሰውነት ክብደቱን ጨምሯል ተብሏል።
ግለሰቡ መጀመሪያ ላይ የሰውነት ክብደቱ ለውትድርና ዝግጁ ነበር የተባለ ሲሆን በሁለተኛ ዙር ላይ በተደረገለት ምርመራ የሰውነት ክብደቱ ከ100 ኪሎ ግራም በላይ ሆኖ ተገኝቷል።
እንደ ኮሪያ ሄራልድ ዘገባ ከሆነ ግለሰቡ ሰውነቱ እንዲጨምሩ የሚያደርጉ ምግቦችን አዘውትሮ ይመገብ እንደነበር ተገልጿል።
ብሔራዊ ሀላፊነት ላለመወጣት ሆን ብሎ ክብደት ጨምሯል የሚል ክስ የቀረበበት ይህ ሰውም ክሱን ክዶ ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱም በግለሰቡ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን ምንም እንኳን ሆን ብሎ ክብደት የጨመረ እና የሀገሪቱን ጦር መቀላቀል ባይችልም ለአንድ ዓመት በመንግስት ተቋማት ውስጥ ማህበራዊ አገልግሎት እንዲሰጥ ታዟል።
ግለሰቡ ለፈጸጸመው ድርጊት በአንድ ዓመት የገደብ እስር እንዲሁም ክብደት እንዲጨምር ምክር ለግሷል የተባለው ደግሞ የስድስት ወር ገደብ እስር በፍርድ ቤት ተላልፎባቸዋል።
ደቡብ ኮሪያ ከጎረቤቷ ሰሜን ኮሪያ ጋር ያላት ግንኙነት መጥፎ የሚባል ደረጃ ላይ ስትሆን ሁለቱም ሀገራት በዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት ላይ ተቃራኒ አቋም ይዘዋል።
10 ሺህ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ወደ ሩሲያ ገብተዋል የተባለ ሲሆን ደቡብ ኮሪያ ደግሞ ለዩክሬን የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ሰጥታለች።