ወታደራዊ ህግ ያወጁትን የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝደንት ከስልጣን ለማገድ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ሳይጸድቅ ቀረ
ምክረ ሀሳብ ያልጸደቀው የፕሬዝደንቱ ፖርቲ ድምጽ ከመስጠት ራሱን በማግለሉ ምክንያት ነው
ዩን ጸረ "ደቡብ ኮሪያ የሆኑ ኃይሎችን" እና አጥፊ ተቃዋሚዎችን ለማጥፋት በሚል ማክሰኞ እለት ያወጁት ወታደራዊ አዋጅ ሀገሪቱን አስደንግጧል
ወታደራዊ ህግ ያወጁትን የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝደንት ዩን ሱክ ዮኦሎ ከስልጣን ለማገድ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ሳይጸድቅ ቀረ።
ፕሬዝደንቱ በዚህ ሳምንት ያወጁትን ለአጭር ጊዜ የቆየውን ወታደራዊ ህግ (ማርሻል ለው) ተከትሎ ተቃዋሚዎች በሚቆጣጠሩት ፖርላማ በዛሬው እለት የቀረበባቸው የእግድ ምክረ ሀሳብ አለመጽደቁን ሮይተርስ ዘግቧል።
ምክረ ሀሳብ ያልጸደቀው የፕሬዝደንቱ ፖርቲ ድምጽ ከመስጠት ራሱን በማግለሉ ምክንያት መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል።
የተሰጠው ድምጽ 195 ብቻ ሲሆን ይህም ከሚያስፈልገው 200 ድምጽ በታች ሆኖ ተመዝግቧል።
"በዚህ በናሽናል አሴምብሊ የተላለፈውን ውሳኔ ሁሉም ህዝብ እያየው ነው። አለም እያየ ነው" ሲሉ የናሽናል አሴምብሊ አፈጉባኤ ው ዎን ሺክ ተናግረዋል።
አፈ ጉባኤው "ምርጫ እንኳን አለመካሄዱ የሚያሳዝን ነው" ብለዋል።
የሀገሪቱ ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ የእግዱን ምክረሀሳብ በድጋሚ የማቅረብ ሀሳብ እንዳለው ገልጿል።
ዩን ጸረ "ደቡብ ኮሪያ የሆኑ ኃይሎችን" እና አጥፊ ተቃዋሚዎችን ለማጥፋት በሚል ማክሰኞ እለት ያወጁት ወታደራዊ አዋጅ ሀገሪቱን አስደንግጧል።ዮን ቆየት ብለው አዋጁን ሰርዘውታል።
ዩን አዋጅ በማወጃቸው ይቅርታ ቢጠይቁም፣ ከሰልጣን ለመልቀቅ ግን ፈቃደኛ አይደሉም።