ደቡብ ሱዳን ከአማጺ ቡድኖች ጋር ስታደርግ የነበረውን የሰላም ድርድር አቋረጠች
ሀገሪቱ በሮም ካቶሊካዊ ማህበር አደራዳሪነት የሚካሄደውን ውይይት አማጺዎች ለጦርነት ጊዜ መግዣ እየተጠቀመበት ነው በሚል ነው ድርድሩን ያቋረጠችው
የደቡብ ሱዳን መንግስት ባለፈው ዓመት ከድርድሩ ራሱን አግልሎ ነበር
የደቡብ ሱዳን መንግስት አማጺ ቡድኖች ድርድሩን "ለጦርነት ጊዜን መግዣ" እየተጠቀሙ ነው በሚል ከሰላማዊ ድርድር ራሱን አግልሏል።
ለአምስት ዓመታት የዘለቀውን የእርስ በርስ ጦርነት ይቋጫል የተባለው የ2018 የሰላም ስምምነትን ያልተፈራረመው ሁለቱ ወገኖች በሮም ካቶሊካዊ ማህበር አደራዳሪነት የተካሄደ ነው ተብሏል።
ድርድሩ በፈረንጆቹ በ2019 የተጀመረ ቢሆንም በደቡብ የሀገሪቱ ክፍል ያለውን ሁከት መግታት አልቻለም። ይሁን እንጂ መንግስትና አማጺዎች በጥር 2020 የተኩስ አቁም ስምምነት ፈርመዋል።
የደቡብ ሱዳን የፕሬዝዳንት ጉዳዮች ሚንስትር ባርናባ ማሪያል ቤንጃሚን ከቀናት በፊት በጻፉት ደብዳቤ መንግስት "በሮም የሰላም ድርድር ላይ ተሳትፎውን አግዷል" ብለዋል።
"በአገራችን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ከተቃዋሚ ቡድኑ ጋር ጠንከር ያለ ውይይት ለማድረግ በዝግጅት ላይ እያለን ይህ ቡድን ውይይቱን ለጦርነት ጊዜ መግዣ እየተጠቀመበት እንደሆነ ደርሰናል" ብለዋል።
መንግስት ባለፈው ዓመት ከድርድሩ ራሱን አግልሎ የነበረ ሲሆን ከቡድኖቹ አንዱ የሆነው ግንባር በደቡብ የሀገሪቱ ክፍል ያላሰለሰ ጥቃት ፈጽሟል ሲል መክሰሱን አል አረቢያ ዘግቧል።
በነሐሴ ወር ግን ውይይቶችን ለመቀጠል ዝግጁ ነኝ ብሏል።
በፈረንጆቹ 2011 ሱዳን ነፃነቷን ካገኘች በኋላ ወደ 400 ሽህ የሚጠጉ ሰዎችን የገደለው የእርስ በርስ ጦርነትን ጨምሮ የአለም አዲሲቷ ሀገር በከባድ አለመረጋጋት ተሰቃይታለች።
በፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና ምክትላቸው ሪክ ማቻር መካከል ከተደረሰው የሰላም ስምምነት በኋላ ሀገሪቱ የተፈጥሮ አደጋዎችን እና የምጣኔ-ሀብተሰ ቀውስን አስተናግዳለችም።
የፖለቲካ ሽኩቻው ለተጨማሪ ብጥብጥ እና በስምምነቱ ላይ የሚደረገውን መሻሻል እያደናቀፈ ነውም ተብሏል።
በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወደ ስምንት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ወይም ሁለት ሶስተኛው የሀገሪቱ ህዝብ ለከባድ ረሃብ የተጋለጡ መሆናቸውን አስጠንቅቋል።