ደቡብ ሱዳን በፌስቡክ እና ቲክቶክ ላይ ጥላው የነበረውን እገዳ አነሳች
በመላ ሀገሪቱ የበቀል ግድያ እንዲቀሰቀስ ያደረገው ዘግናኝ ቪዲዮ ከማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲወርድ መደረጉን የብሔራዊ ኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን ገልጿል
ደቡብ ሱዳን ከበርካታ አስርት አመታት ጦርነትና ደም መፋሰስ በኋላ በ2012 ከሱዳን ተገንጥላ ነጻ ሀገር መሆኗ ይታወሳል
ደቡብ ሱዳን በፌስቡክ እና ቲክቶክ ላይ ጥላው የነበረውን እገዳ አነሳች።
የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ደቡብ ሱዳን ውስጥ የሱዳን ዜጎች ሲገደሉ የሚያሳዩ ቪዲዮዎች መሰራጨታቸውን ተከትሎ በፌስቡክ እና ቲክቶክ ላይ ጥለውት የነበረውን ጊዜያዊ እግድ አንስተዋል።
በመላ ሀገሪቱ የበቀል ግድያ እንዲቀሰቀስ ያደረገው ዘግናኝ ቪዲዮ ከማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲወርድ መደረጉን የብሔራዊ ኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን በትናንትናው እለት ለቴለኮሞች እና የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጭዎች በጻፈው ደብዳቤ ገልጿል።
"በደቡብ ሱዳን ከማህበራዊ ሚዲያ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ ችግሮች መጨመር የማህበረሰቡን መብት ከመጠበቅ ጎንለጎን የግጭቱን መነሻ መፍታተ እንደሚያስፈልግ የሚያሳይ ነው" ሲሉ የብሔራዊ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ናፖሊዮን አዶክ ጋይ በደብዳቤው ገልጸዋል።
የመብት ተሟጋቾች የሱዳን ጦርና አጋሮቹ የኢል ገዚራ ግዛት ዋና ከተማ ዋድ መዳኒን ከተቆጣጠሩ በኋላ በዚህ ወር መጀመሪያ ጎሳን መሰረት ያደረገ ግድያ ፈጽመዋል ሲሉ ከሰዋቸዋል። የሱዳን ጦር ግለሰቦች የፈጸሙትን የደቡብ ሱዳኑን ግድያ አውግዟል።
ደቡብ ሱዳን ከበርካታ አስርት አመታት ጦርነትና ደም መፋሰስ በኋላ በ2012 ከሱዳን ተገንጥላ ነጻ ሀገር መሆኗ ይታወሳል።