የሰላም ስምምነቶች መቋጫ እንዲያገኙ የፓርላማ አባላቱ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ፕሬዚዳንት ሳለቫ ኪር ጥሪ አቅርበዋል
ከ10 ዓመታት በፊት የተመሰረተችው ደቡብ ሱዳን በታሪኳ ለመጀመርያ ጊዜ ሴት የፓርላማ አፈ-ጉባኤ መሰየሟ ተነግሯል።
የሀገሪቱን ፓርላማ እንዲመሩ በፕሬዚዳንት ሳልቫኪር አማካኝት የተሾሙት የሀገሪቱ ፓርላማ ሴት አፈ ጉባኤ ጄማ ኑን ኩምባ ናቸው።
ፕሬዝዳንቱ በጁባ በተካሄደው የፓርቲያቸው ጠቅላላ ጉባኤ " ቀጣይዋ የፓርላማው አፈ ጉባኤ ኩምባ ይሆናሉ" ሲሉም ይፋ ማድጋቸውን ኤ.ኤፍ.ፒ ዘግቧል።
የፕሬዝዳነቱ ሹመት በፓርላማ አባለቱ ድጋፍና ጭብጨባ የታጀበ እንደነበርም ነው የተገለጸው።
አዲሷ አፈ ጉባዔ ኩምባ የደቡብ ሱዳ የሰላም ስምምነትን የማስፈጻም ትልቅ ኃላፊነት እንደተጣለባቸውንም ነው የኤ.ኤፍ.ፒ ዘገባ የሚያመለክተው።
እንደፈረንጆቹ 1966 የተወለዱት አዲስቷ አፈ-ጉባኤ ኩምባ 1990ዎቹ መጀመርያ ላይ የሱዳን ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄን /SPLM/ እንደተቀላቀሉ ይነገርላቸዋል።
ከዛም በኋላ ቢሆን ኩምባ በፓርቲው የነበራቸው ሚና በጊዜ ሂደት እየጎላ በመምጣቱ በቀድሞ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ይመራ በነበረው የኤስ.ፒ.ኤል.ኤም እና የሱዳን መንግስት የሰላም ድርድር ሲሳተፉ የቆዩ ናቸው።
ኩምባ መሾማቸውን ተከትሎ " የፓለቲካ ጥሪው ተቀብሎ የጋራ ዓላማ የማሳካቱ ኃላፊነት ለኔ ቀላል የሚባል አይሆንም" ሲሉ ተደምጠዋል።
ሳልቫኪር በበኩላቸው የተቀሩት የሰላም ስምምነቶች መቋጫ እንዲያገኙ ኩምባም ሆነ የፓርላማ አባላቱ ኃላፊነታቸው እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
"የሰላም አምባሳደሮች መሆን አለባችሁ"ም ብሏል ፕሬዝዳንት ኪር።
ደቡብ ሱዳን ነጻነቷን ካገኘችበት ጊዜ አንስቶ በቀውስ የታጀበ ጉዞ ስታደርግ የቆየች ሲሆን፤ 60 በመቶ የሚሆነው ህዝቧ በከፍተኛ የምግብ እጥረት አደጋ ላይ እንደሚገኝ የዓለም ምግብ ፕሮግራም መረጃዎች ይጠቁማሉ።