የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን ከስልጣን አነሱ
ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር የአገሪቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቤትሪስ ካሚሻን ከስልጣን አባረዋል
ፕሬዝዳንቱም በምትካቸው ማይክ አይ ዴንግስን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድርገው ሾመዋል
የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ከስልጣን አነሱ።
የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩትን በድንገት ከስልጣን ማንሳታቸውን አስታውቀዋል።
ለአንድ ዓመት ያክል የደቡብ ሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ቤትሪስ ካሚሻ ከስልጣን መነሳታቸውን የአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸውን ለምን ከስልጣን እንዳነሷቸው እስካሁን የወጣ መረጃ አለመኖሩንም ዘገባው አክሏል።
ከስልጣን በተነሱት ሚኒስትር ቦታ ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ማይክ አይ ዴንግን የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተደርገው መሾማቸው ተገልጿል።
አዲሱ የደቡብ ሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአገሪቱ ፕሬዘዳንት ጽህፈት ቤት በተለያዩ የስራ ዘርፎች በሀላፊነት ሰርተዋል ተብሏል።
ደቡብ ሱዳን በፈረንጆቹ 2018 ዓመት በአዲስ አበባ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት አሁን ላይ በመተግበር ላይ ስትሆን ሁሉን አካታች የደቡብ ሱዳን የሽግግር መንግስት በማስፈጸም ላይ መሆኗ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከስልጣን መነሳት ምክንያት ሊሆን ይችላል የሚሉ መላምቶች በመነሳት ላይ ናቸው።
ከ11 ዓመት በፊት በህዝበ ውሳኔ ከሱዳን ነጻነቷን ያገኘችው ደቡብ ሱዳን በፈረንጆቹ 2013 ዓመት አንስቶ በእርስ በርስ ጦርነት ስተታመስ ቆይታለች።
ይሄንን ተከትሎም በ10 ሺዎች ደቡብ ሱዳናዊያን ህይወታቸውን ሲያጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ወደ ኢትዮጵያ እና ዩጋንዳ መሰደዳቸውን የመንግስታቱ ድርጅት ሪፖርት ያስረዳል።