የኢትዮጵያ መንግስት ደህንነት አማካሪ የሆኑት አቶ ገዱ ከደቡብ ሱዳን የደህንነት አማካሪ ጋር መክረዋል
የኢትዮጵያ መንግስት ደህንነት አማካሪ የሆኑት አቶ ገዱ ከደቡብ ሱዳን የደህንነት አማካሪ ጋር መክረዋል
ደቡብ ሱዳን በየትኛውም አጋጣሚ ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን መቆሟን አስታወቀች፡፡ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ የደህንነት አማካሪ ገዱ አንዳርጋቸው ዛሬ በጁባ ተወያይተዋል፡፡
ሀገራቸው ሉዓላዊ ሆና ቆመችው ኢትዮጵያ በሰራችው ሥራ መሆኑን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ ጁባ ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን መሆኗን ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው መግለጻቸውን በሀገሪቱ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቋል፡፡
አቶ ገዱ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ ሕግ የማስከበርና ሉዓላዊነቷን የማስከበር ሥራዋን እየሰራች መሆኑን ለደቡብ ሱዳን መንግስት አስረድተዋል፡፡
ሕግ የማስከበሩና ሉዓላዊነትን የማስጠበቁ ሥራ የመንግስት ግደታ መሆኑን ያነሱት አቶ ገዱ ይህ በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃል ማለታቸውን ኤምባሲው አስታውቋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ የደህንነት አማካሪ በጁባ ቆይታቸው ከደቡብ ሱዳኑ ደህንነት ኃላፊ ጀነራል አኮል ኮር እና በጁባ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ጋር መገናኘታቸው ተገልጿል፡፡
አቶ ገዱ ለከሰሞኑ በጅቡቲና በሞቃዲሾ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በጣሊያንና በቤልጀም ከሀገራትና ተቋማት መሪዎች መሪዎች ጋር መወያየታቸው ይታወሳል፡፡