የደቡብ ሱዳናውያን አማካይ በህይወት የመኖር እድሜ ጣሪያ በምስራቅ አፍሪካ ዝቅተኛው ነው ተባለ
የሩዋንዳውያን አማካይ በህይወት የመኖር እድሜ ጣሪያ 69.6 አመት በምስራቅ አፍሪካ ከፍተኛው ነው
የዓለም ባንክ አኃዛዊ መረጃ የደቡብ ሱዳናውያን አማካይ የመኖር እድሜ ጣሪያ 55 አመት መሆኑ ያመለክታል
የደቡብ ሱዳናውያን አማካይ በህይወት የመኖር እድሜ ጣሪያ በምስራቅ አፍሪካ ካሉ ሀገራት ዝቅተኛው ነው ተባለ፡፡
የዓለም ባንክ አኃዛዊ መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ ከ1960 እስከ 2020 የነበረው የደቡብ ሱዳናውያን አማካይ የመኖር እድሜ ጣሪያ 55 አመት ነው፡፡
በሌላ በኩል የማክሮ-ትሬንድስ መረጃ እንደሚያሳየው የደቡብ ሱዳናውያን አማካይ በህይወት የመኖር እድሜ ጣሪያ በ2023 ወደ 58.7 አመት ከፍ ብሏል፡፡
ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት የሚደረገው የጤና እርዳታ መርሃ ግብር ተደራሽነት መስፋፋቱ ፤ እንደ ደቡብ ሱዳን ባሉ ሀገራት ላይ ያለው አማካይ የህይወት እድሜ ጣሪያ እየጨመረ ለመምጣቱ ምክንያት መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሩዋንዳውያን አማካይ በህይወት የመኖር እድሜ ጣሪያ በምስራቅ አፍሪካ የተሻለ መሆኑ የዓለም ባንክ አሃዛዊ መረጃ ያመለክታል፡፡
እንደፈረንጆቹ በ2022 በተደረገው አምስተኛው የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ መረጃ መሰረት የሩዋንዳ ዜጎች አማካይ የህይወት እድሜ በ2002 ከነበረው የ51.2 አመት የእድሜ ጣሪያ በ18 አመታት ጨምሮ ወደ 69.6 አመት ከፍ ብሏል።
ከሩዋንዳውያን ቀጥሎ ታንዛንያውያን (በ66 አመታት) ፣ኬንያ እና ዩጋንዳ (በ63 አመታት)፣ ብሩንዲያውያን (በ61 አመታት) ፣ እንዲሁም የዲሞክራቲክ ኮንጎ ዜጎች (በ60 አመታት) በቀጠናው የእድሜ ጣሪያቸው ከፍተኛ የሆኑ ናቸው።